ለጉብኝት ወደ ሌላ ሀገር የሄዱት ፕሬዝደንት በውሻ መነከሳቸው አነጋገረ
በውሻ ንክሻ የደረሰባቸው ፕሬዝደንት የኦስትሪያ ፕሬዝደንት ናቸው።
የኦስትሪያው ፕሬዝደንት ውሻውን ለማሻሸት ጎንበስ በሚሉበት ወቅት እጃቸውን ነክሷቸዋል
ለጉብኝት ወደ ሌላ ሀገር የሄዱት ፕሬዝደንት በውሻ መነከሳቸው አነጋገረ ሆኗል።
በውሻ ንክሻ የደረሰባቸው ፕሬዝደንት የኦስትሪያ ፕሬዝደንት ናቸው።
እንደስካይ ኒውስ ዘገባ ፕሬዝዳንቱ ለይፋዊ ጉብኝት በሞልዶቫ በተገኙበት ወቅት የጓደኝነት ህግን የጣሰው የሞልዶቫ 'የመጀመሪያ ውሻ' እጃቸውን ነክሶ ጉዳት አድርሶባቸዋል።
ነገርግን የውሻው ድርጊት የኦስትሪያውን ፕሬዝደንት አሌክሳንደር ቫንደር ቤለን እና የሞልዶቫውን ፕሬዝደንት ማይ ሳንዱን ግንኙነት አላሻከረውም።
ኘሬዝደንት ቫንደር ቤለን ይቅር ብለዋል።
ባለፈው አርብ በሀገሪቱ ሚዲያዎች የተለቀቁ ተንቀሳቃሽ ምስሎች እንደሚያሳዩት ቫኔደር ቤለን ከሳንዱ ጋር በሞልዶቫ ዋና ከተማ ቺሲናው ጋር ቆመው ታይተዋል።
የኦስትሪያው ፕሬዝደንት ውሻውን ለማሻሸት ጎንበስ በሚሉበት ወቅት እጃቸውን ነክሷቸዋል።
ፕሬዝደንት ሳንዱ በውሻቸው ድርጊት በእንግሊዘኛ ቋንቋ ይቅርታ ጠይቀዋል፣ ውሻው ይህን ያደረገው በአቅራቢያው ሰው ሲበዛ በመፍራቱ ምክንያት ነው ሲሉም አብራርተዋል።
ቫንደር ቤለን በሚቀጥለው ስብሰባ ላይ እጃቸው በፋሻ ተጠቅልሎ ከሞልዶቫ ፖርላማ አፈጉባኤ ጋር ታይተዋል። ቢሯቸው "በፋሻ የሚድን ትንሽ ቁስል ነው" ብሏል። ፕሬዝደንቱ በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙም ቢሮው አክሏል።
ቫንደር ቤለን ከሳንዱ እና ከስሎቨንያን ፕሬዝደንት ናታሳ ፒሮክ ሙሳር ጋር በሞልዶቫ የአውሮፖ ህብረት አባልነት ጥያቄ ጉዳይ ተወያይተዋል።
የኦስትሪያው ፕሬዝደንት ንክሻው ከደረሰባቸው በኋላ በኢንስታግራም ገለጻቸው ትንሽ ችግር ፈጥሮ ነበር ብለዋል።
ውሻ እንደሚወዱ የገለጹት ቫንደር ቤለን ውሻው ሰው ሰለበዛበት ተቆጥቶ ነበር ብለዋል።