የፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ውሻ በተደጋጋሚ ደህንነቶችን መንከሱ ተከለጸ
"ኮማንደር" የተሰኘው የፕሬዝዳንት ባይደን ውሻ 11የፕሬዝዳንቱን ጠባቂዎች ነክሷል ተብሏል
የጀርመን ዝርያ ያለው ይህ ውሻ በነጩ ቤተመንግስት ውስጥ አሳሳቢ ጉዳይ መሆኑ ተገልጿል
የፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ውሻ በተደጋጋሚ የፕሬዝዳንቱን ደህንነቶች መንከሱ ተከለጸ።
ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ዝርያው የጀርመን ሼፐርድ የሆነ ውሻ ያላቸው ሲሆን "ኮማንደር" የሚል ስምም ተሰጥቶታል።
የሁለት ዓመት ከግማሽ እድሜ ያለው ይህ ውሻ የፕሬዝዳንት ባይደን እና ቤተሰባቸው ንብረት እንደሆነ ተገልጿል።
ይሁንና ይህ ውሻ የፕሬዝዳንቱን ጠባቂዎች በተደጋጋሚ ነክሷል የተባለ ሲሆን በትናንትናው ዕለትም አንድ ደህንነት መነከሱን ሲኤንኤን ዘግቧል።
ውሻው ወደ ነጩ ቤተ መንግሥት ከገባበት ጊዜ ጀምሮም በ11 ሰዎች ላይ ንክሻ መፈጸሙ ተገልጿል።
በዚህ ውሻ ንክሻ የተማረሩ የፕሬዝዳንቱ ቤተሰቦች እና የነጩ ቤተ መንግሥት ጠባቂዎች ቅሬታ አቅርበዋል ተብሏል።
ትናንት ንክሻ የተፈጸመበት ደህንነት እንዳለው ፕሬዝዳንት ባይደን ውሻውን መቆጣጠር አልቻሉም፣ እኔም ከንከሻው ማምለጥ አልቻልኩም ሲል ተናግሯል።
በ"ኮማንደር" ላይ የቀረበውን ተደጋጋሚ ክስ ተከትሎም ውሻው ከነጩ ቤተ መንግሥት ወደ ሌላ የፕሬዝዳንቱ ቤተሰብ ተዛውሯል ተብሏል።
ይህ ሞገደኛ ውሻ ወደ ነጩ ቤተ መንግስት እንዲገባ የተደረገው በፈረንጆቹ በ2021 ላይ የፕሬዝዳንት ባይደን ወንድም ጄምስ በስጦታ መልክ ካበረከተ በኋላ እንደሆነ በዘገባው ላይ ተጠቅሷል።