ደቡብ ኮሪያ የውሻ ስጋ እንዳይበላ ልታግድ ነው ተባለ
የውሻ ስጋ መብላት በኮሪያ ባህረ ሰላጤ የቆየ ልምድ ነው
ረቂቅ ህጉ በውሻ ስጋ ምርት ለተሰማሩ ኢንዱስትሪዎች የሶስት አመት የእፎይታ ጊዜ እና የፋይናንስ ድጋፍ እንዲያገኙ ያስችላቸዋል
ደቡብ ኮሪያ የውሻ ስጋ እንዳይበላ ልታግድ ነው ተባለ።
ደቡብ ኮሪያ የውሻ ስጋ እንዳይበላ ክልከላ በመጣል የሀገሪቱ ጥንታዊ ልምድ እንዲያበቃ የማድረግ እቅድ እንዳላት የገዥው ፖርቲ የፖሊሲ ኃላፊ ተናግረዋል።
የደቡብ ኮሪያ የውሻ ስጋ t ልምድ ከሀገር ውጭ ከፍተኛ ተቃውሞ ያስነሳ ቢሆንም በሀገር ውስጥም የሚነሳው ተቃውሞ እያየለ መጥቷል።
"የውሻ ስጋ እንዳይበላ ህግ በማውጣት በውሻ ስጋ ጉዳይ ያለውን ማህበራዊ ግጭት እና ውዝግብ የመዝጊያ ጊዜው አሁን ነው" ሲሉ የፖሊሲ ኃላፊው ዩ ኢዩ ዶንግ ከመንግስት ባለስልጣናት እና የእንስሳት መብት ተሟጋቾች ጋር ባደረጉት ስብሰባ ተናግረዋል።
ዩ እንደተናገሩት መንግስት እና ገዥው ፖርቲ በዚህ አመት ክልከላውን ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል ህግ ያወጣል ብለዋል።
የግብርና ሚኒስትሩ ቹንግ ህዋንግ ኪዩን መንግስት ክልከላውን በፍጥነት ተግባራዊ እንደሚያደርግ እና በውሻ ስጋ ምርት ለተሰማሩ ኢንዱስትሪዎች ንግዳቸውን ሲዘጉ የሚችለውን ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል።
ከዚህ ቀደም የቀረቡ የጸረ-ውሻ ስጋ ረቂቅ ህጎች ያልጸደቁት በዘርፉ የተሰማሩ ኢንዱስትሪዎች ባቀረቡት ተቃውሞ እና የውሻ ስጋ በሚያመርቱ አርሶ አደሮች እና በሬስቶራንቶች ስጋት ምክንያት ነበር።
ረቂቅ ህጉ በውሻ ስጋ ምርት ለተሰማሩ ኢንዱስትሪዎች የሶስት አመት የእፎይታ ጊዜ እና የፋይናንስ ድጋፍ እንዲያገኙ ያስችላቸዋል።
የውሻ ስጋ መብላት በኮሪያ ባህረ ሰላጤ የቆየ ልምድ ነው።
አሁን ላይ የውሻ ስጋ በብዙ ሬስቶራንቶች የሚገኝ እና በትላልቅ ሰዎች የሚዘወተር ቢሆንም እንደ ድሮው በብዛት አይበላም።
በደቡብ ኮሪያ 1150 የውሻ እርባታ ጣቢያዎች፣ 34 ቄራዎች፣ 219 የሚያሰራጩ ድርጅቶች እና የውሻ ስጋ የሚያቀርቡ 1600 ሬስቶራንቶች መኖራቸውን የሀገሪቱ መንግስት መረጃ ያሳያል።