ኦስትሪያዊው ተጨዋች በዓለም አቀፍ ጨዋታ ፈጣኗን ግብ አስቆጠረ
የባውምጋርነር ግብ በ1993ቱ የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ የሳን ማሪኖው ዴቪድ ጓልቲየሪ በእንግሊዝ ላይ ካስቆጠራት ግብ በሁለት ሰከንድ ትቀድማለች
ኦስትሪያ ስሎቫኪያን ባሸነፈችበት ጨዋታ ባውምጋርነር በዓለም አቀፍ ጨዋታ ፈጣኗን ግብ በስድስተኛው ሰከንድ አስቆጥሯል
ኦስትሪያዊው ተጨዋች በዓለም አቀፍ ጨዋታ ፈጣኗን ግብ አስቆጠረ።
ኦስትሪያ ስሎቫኪያን ባሸነፈችበት ጨዋታ ክሪስቶፍ ባውምጋርነር በዓለም አቀፍ ጨዋታ ፈጣኗን ግብ በስድስተኛው ሰከንድ ማስቆጠሩን ቢቢሲ ስፖርት ዘግቧል።
የ24 አመቱ አማካኝ ተጨዋች ሶስት ተከላይካዮችን በማለፍ ግብ ጠባቂውን ማርቲን ዱብሬቭካን ሸውዶ ግብ ማስቆጠር መቻሉን ዘገባው ጠቅሷል።
የባውምጋርነር ግብ በ2013 የጀርመኑ ሉካስ ፖዶስኪይ በኢኳዶር ላይ ካስቆጠራት ግብ የፈጠነች ነች።
አንድሬስ ዌንማን ዘግይቶ ያስቆጠራት ግብ የራልፍ ራንግኒክ ቡድን አሸናፊነትን አረጋግጣለች።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ባለፈው ማክሰኞ በቬና ቱርክን ያስተናገደችው ኦስትሪያ አራት ተከታታይ ጨዋታዎችን በማሸነፏ በክረምት በጀርመን ለሚካሄደው የአውሮፖ ዋንጫ ለማለፍ ነጥብ እያከማቸች ነው።
የኦስትሪያ ደጋፊዎች ባውምጋርነር ባሳየው አፈጻጸም ደስታቸውን ገልጸዋል።
የባውምጋርነር ግብ በ1993ቱ የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ የሳን ማሪኖው ዴቪድ ጓልቲየሪ ጨዋታው ከተጀመረ ከስምንት ደቂቃ በኋላ በእንግሊዝ ላይ ካስቆጠራት ግብ በሁለት ሰከንድ ትቀድማለች።
በ2019 የሳውዝሀምፕተኑ ሻን ሎንግ በዋትፎርድ ላይ በ7.69 ሰከንድ ላይ ያስቆጠራት ግብ በፕሪሚየር ሊግ ታሪክ ፈጣን ኳስ ተብላ ተመዝግባለች።
በመጋቢት ውስጥ ሮይ ማካይ በመጨረሻ 16ቱ ጨዋታ ወቅት ለባየር ሙኒክ በሪያል ማድሪድ ላይ በ10.2 ሰከንድ ግብ በማስቆጠር ሌላ ፈጣን የሚባል ግብ ማስቆጠሩ ይታወሳል።
ባለፈው የካቲት በእንግሊዝ በተካሄደ የከፍተኛ ሊግ ጨዋታ የክሮይዶን ኤፍሲው ርያን ሀል በኮክፎስተር ላይ በ2.31 ሰከንድ ላይ አስቆጥሮ የነበረ ቢሆንም ጊኒየስ ወርልድ ሪከርድስ ከፕሮፌሽናል ሊግ ውጭ ያሉ ጨዋታዎችን ስለማይከታተል ግቧን በሪከርድ አልመዘገባትም።