ለአራት ዓመት የታገደው ፖል ፖግባ ወደ እግር ኳስ የመመለስ እድል አለው?
የዓለም ዋንጫ አሸናፊው ፖል ፖግባ አነቃቂ ንጥረ ነገሮችን ተጠቅሞ መገኘቱ ተረጋግጧል
ተጫዋቹ እስከ ነሀሴ 2019 ዓ.ም ድረስ ከእግር ኳስ ውድድሮች ታግዷል
ፖል ፖግባ አበረታች ንጥረ ነገሮችን ሆን ብሎ አለመውሰዱን ካስረዳ የአራት ዓመት እገዳው ሊቀንስለት ይችላል ተባለ፡፡
የዓለም ዋንጫ አሸናፊው ፈረንሳዊው ፖል ፖግባ አነቃቂ ንጥረ ነገሮችን ተጠቅሞ በመገኘቱ ለአራት ዓመታት ከእግር ኳስ ውድድሮች መታገዱ ተገልጿል፡፡
የቀድሞው የማንችስተር ዩናይትድ ክለብ ተጫዋች አበረታች ንጥረ ነገሮችን ተጠቅሞ የተገኘው በተደረገለት ምርመራ አማካኝነት እንደሆነ ስካይ ስፖርት ዘግቧል፡፡
እንደዘገባው ከሆነ በምህጻረ ቃሉ ዋዳ የተሰኘው ዓለም አቀፉ የጸረ አበረታች ንጥረ ነገሮች ተቋም ባደረገው ሁለት ጊዜ ምርመራ ለስፖርተኞች የተከለከለ ንጥረ ነገር ተጠቅሞ ተገኝቷል፡፡
በዚህም ምክንያት እስከ ነሀሴ 2019 ዓ.ም ድረስ ከእግር ኳስ ውድድሮች ተሳትፎ የታገደ ሲሆን ተጫዋቹ ውሳኔውን ከተቃወመ ይግባኝ የመጠየቅ መብት እንዳለውም ተገልጿል፡፡
የ34 ዓመቱ የጁቬንቱስ ተጫዋች ፖል ፖግባ አበረታች ንጥረ ነገሮች ተጠቅሟል የሚለው ቅድመ ምርመራ ከተገኘበት ጊዜ ጀምሮ ከእግር ኳስ ታግዶ ቆይቷል፡፡
ታዋቂው የእግር ኳስ አሰልጣኝ ኤሪክሰን በህይወት የመቆየት እድሉ ለወራት ብቻ እንደሆነ ተናገረ
የጣልያን እግር ኳስ ፌዴሬሽንም የዋዳን ውሳኔ እንደሚቀበል እንደሚተገብር አስታውቋል፡፡
ተጫዋቹ ፖል ፖግባ በከከሉሉ የዋዳን ውሳኔ በመቃወም ሉሳን ወደ ሚገኘው ዓለም አቀፉ የሰፖርት ግልግል ዳኝነት ወይም ካስ ይግባኝ ሊጠይቅ እንደሚችል በዘገባው ለይ ተጠቅሷል፡፡
ክለቡ ጁቬንቱስ እስካሁን በጉዳዩ ዙሪያ አስተያየት ከመስጠት የተቆጠበ ሲሆን ካሳለፍነው መስከረም ጀምሮ የተጫዋቹን ግልጋሎት በጉዳት እና በውሳኔው ምክንያት ሳይገኝ ቆይቷል፡፡
ፖል ፖግባ ብዙ ሆርሞን እንዲመረቱ ያደረግላ በሚል የሚታወቀው በምህጻረ ቃሉ ዲኤችኢኤ የተሰኘውን አነቃቂ መድሃኒት መውሰዱ በምርመራ መረጋገጡ ተገልጿል፡፡
ተጫዋቹ ንጥረ ነገሩን ሆን ብሎ እንዳልወሰደ ማስረዳት ከቻለ የአራት ዓመት እገዳው ሊቀንስለት እንደሚችል ባለሙያዎች በመናገር ላይ ናቸው፡፡