በ2023 ከፍተኛ ተከፋይ የሆኑ የእግርኳስ ተጨዋቾች እነማን ናቸው?
ከፒኤጂ ወደ አሜሪካው ኢንተር ሚያሚ ክለብ የተቀላቀለው ሜሲ 135 ሚሊዮን ዶላር በአመት ይከፈለዋል
ለሳኡዲ ፕሮሊጉ አል ናስር የሚጫወተው ሮናልዶ በ260 ሚሊዮን ዶላር ቁጥር አንድ ተከፋይ መሆኑን ፎርብስ ገልጿል
ፖርቹጋላዊው ክርስቲያኖ ሮናልዶ በፈረንጆቹ 2023 የዓለም ቁጥር አንድ ተከፋይ ተጨዋች መሆኑን ፎርብስ መጽሄት ያወጣው መረጃ ያመለክታል።
እንደ ፎርብስ ዘገባ ከሆነ ሮናልዶ በ260 ሚሊዮን ዶላር አመታዊ ክፍያ ያገኛል።
ሮናልዶ ቁጥር አንድ ተከፋይ ተጨዋች መሆን የቻለው ከአውሮፓ በሳኡዲ አረቢያው ፕሮሊግ ስር ላለው የአል ናስር ክለብ መፈረሙን ተከትሎ ነበር።
የአምስት ጊዜ ባሎንዶኦር ሽልማት አሸናፊው ክርስቲያኖ ሮናልዶ በፈረንዶቹ 2022 በአል ናስር ለሁለት አመት ተኩል የሚያቆየውን ኮንትራት መፈረሙ ይታወሳል።
አልናስር ሮናልዶን ለማስፈረም ምን ያህል ገንዘብ እንዳወጣ ይፋ ባያደርግም፣ሚዲያዎች ግን በ214 ሚሊዮን ዶላር ኮንትራት መፈሙን በወቅቱ ዘግበዋል።
አል ናስር ሮናልዶን ማስፈረም መቻሉ ለክለቡ ታሪካዊ መሆኑን እና የሳኡዲ ፕሮ ሊግንም እንደሚያነቃቃ ገልጾ ነበር።
የሮናልዶን መፈረም ተከትሎ በርካታ የአውርሮፓ ተጨዋቾች ለሳኡዲ ፕሮሊግ ክለቦች ፈርመዋል።
ሮናልዶን ተከትሎ ቁጥር ሁለት ተከፋይ የሆነው ደግሞ የ2022 የኳታር የአለም ዋንጫ አሸናፊው አርጀንቲናዊው ኮከብ ሊዮነል ሜሲ ነው።
ከፓሪስ ሴንት ጀርሜን (ፒኤጂ) ወደ አሜሪካው ኢንተር ሚያሚ ክለብ የተቀላቀለው ሜሲ በአመት 135 ሚሊዮን ዶላር ይከፈለዋል።
በከፍተኛ ተከፋይነት ሶስተኛ ደረጃን የያዘው ደግሞ የሳኡዲ ፕሮሊጉን አል-ሂላል የተቀላቀለው ብራዚላዊው ኮከብ ኔይማር ጁኒየር ነው።
ኔማር 112 ሚሊዮን ዶላር አመታዊ ክፍያ አግኝቷል።
ኔይማርን ያስፈረመው አል-ሂላል በሳኡዲ ፕሮሊግ በተከታታይ 14 ጨዋታዎችን በማሸነፍ አዲስ ሪከርድ ማስመዝገቡን መግለጹ ይታወሳል።
ፎርብስ ተጨዋቾቹ በሚሊዮን ዶላር ምን ያህል እንደሚከፈላቸው በደረጃ እንደሚከተለው አስቀምጧል።
ክርስቲያኖ ሮናልዶ 260
ሊዮነል ሜሲ 135
ኔማር ጁኒየር 112
ክሊያን ምባፔ 110
ካሪም ቤንዜማ 106
ኢርሊንግ ሀላንድ 58
መሀመድ ሳላህ 53
ሳዲኦ ማኔ 52
ኬቪን ዲብሮይና 39
ሀሪ ኬን 36