የ“ባልሽን እንዴት መግደል ትችያለሽ” መጽሃፍ ደራሲ በባሏ ግድያ የእድሜ ልክ አስራት ተፈረደባት
ክራምፕተን ሮቢል ባሏን በጥይት መጥታ እንደገደለችውም ፍርድ ቤት አረጋግጧል
ደራሲዋ “የማይጣጣም ባለቤት” እና “የተሳሳተ ፍቅር” በተሰኙ ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ልብወለድ ድርሰቶቿም ትታወቃለች
ቀደም ሲል “ሃው ቱ መርደር ዩር ሃዝበንድ” የሚል መጽሃፍ ለተደራሲያን ያበረከትቸው ድንቅ የፍቅር ደራሲዋ ክራምፕተን ሮቢል በባሏ ግዲያ የእድሜ ልክ አስራት ተፈረደባት፡፡
የ71 ዓመት ደራሲዋ የ1ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር የኢንሹራንስ ለማግኘት በሚል ለ26 ዓመታት አብሯት የኖረውን ሁለተኛ ባሏ መግደሏ በፍርድ ቤት ተረጋግጧል፡፡
በወንጀል የተገደለው ባሏ ዳንኤል ብሮፊ የተባለ በአንድ ኦሪጎን ውስጥ በሚገኝ ምግብ ቤት ውስጥ ሼፍ ሆኖ ሲያገለግል የነበረ ሰው ነው ተብለዋል፡፡
የክራምፕተን ሮቢል ባል እንደፈረንጆቹ ሰኔ፤2018 በሚሰራበት ኩሽና ቤት ሳለ በሁለት ጥይት ተመትቶ ሞቶ እንደተገኘም ነው ከፖሊስ የተገኘ መረጃ የሚያመላክተው፡፡
ግዲያ በተፈጠመበት ወቅት ክራምፕተን ባለቤቷ ብሮፊ ወደ ስራው በመሄድ ላይ ሳለ በመኪና ውስጥ ሆና እየሰለለችው የሚያሰይ ተንቀሳቃሽ ምስል ተገኝቶ በማስጃነት ለፍርድ ቤት መቅረቡም አሶሼትድ ፕሬስ ዘግቧል፡፡
ፓሊስ፤ ክራምፕተን ባሏን የገደለችበት መሳሪያ ማግኘት ባይችልም ተመሳሳይ ሞዴል ያለው መሳሪያ እንደገዛች ግን አረጋግጫለሁ ብሏል፡፡
ክራምፕተን ፤ ብሮፊ ከሞተበት ሰዓት ጀምሮ " የማስታወስ ችግር እንደገጠማት" በመግለጽ ላይ ናት፡፡
ይሁን እንጂ በመኪና ስትከተለው የሚያሳየውን ተንቀሳቃሽ ምስል መካድ አልቻለችም፡፡
በዚህም 12 ሰዎች የተሰየሙበት ፍርድ ቤት ውሎ፤ ጉዳዩን በዝርዝር ያዳመጠ ሲሆን ከሁለት ቀናት በኋላ ክራምፕተን የባሏ ገዳይ መሆኗ ድምዳሜ ላይ ደርሷል፡፡
በዚህም ፍረድ ቤቱ ክራምፕተን የእድሜ ልክ (25 ዓመት) እስራት ብይን ሰጥቷል፡፡
ክራምፕተን ሮቢል “ሃው ቱ መርደር ዩር ሃዝበንድ” ወይም “ባልሽን እንዴት ትገድሊያለሽ” የተሰኘው መጽሃፏ ከማሳተሟ ቀደም ሲል “የማይጣጣም ባለቤት” እንዲሁም “የተሳሳተ ፍቅር” የተሰኙ ድንቅ ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ልብወለድ ድርሰቶች ለአንባቢያን ማበርከት የቻለች ድንቅ ደራሲ ናት፡፡