በአላስካው የአውሮፕላን መከስከስ አደጋ ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች አስከሬን መገኘቱን ባለስልጣናት ገለጹ
ኤንቲኤስቢ መርማሪዎች በቅርቡ የደረሱትን ሁለት ከባድ አደጋዎች በመመርመር ላይ ይገኛል
![](https://cdn.al-ain.com/images/2025/2/09/243-122817-258-121814-bcd342fa-5a25-4189-a43f-cf6b08d682fc-16x9-1200x676-700x400_700x400.jpeg)
የአውሮፕላን ስብርባሪ በቤሪንግ ባህር በርጋ የበረዶ ግግር ላይ ቢያርፍም፣ የሁሉም ሰዎች አስከሬን መገኘቱንና ማንነታቸው መለየቱን ባለስልጣናት ተናግረዋል
በአላስካው የአውሮፕላን መከስከስ አደጋ ህይወታቸውን ያጡ የሁሉም ሰዎች አስከሬን መገኘቱን ባለስልጣናት ገለጹ።
ባለፈው ሐሙስ ተጋጭቶ የ10 ሰዎችን ህይወት የቀጠፈው የአላስካው ሴስና 208ቢ ግራንድ ካራቫን አውሮፕላን ስብርባሪ በቤሪንግ ባህር በርጋ የበረዶ ግግር ላይ ቢያርፍም፣ የሁሉም ሰዎች አስከሬን መገኘቱንና ማንነታቸው መለየቱን ባለስልጣናት ተናግረዋል።
የኖሜ በጎ በፈቃደኛ የእሳት አደጋ ክፍል በፌስቡክ ገጹ ትናንት ምሽት እንደገለጸው "በቤሪን አውሮፕላን ላይ ተሳፍረው የነበሩ ሰዎች(አስከሬን) ወደ ቤታቸው ተመልሷል።" የአሜራካ የድንበር ጠባቂ(ኮስት ጋርድ)፣ የአሜሪካ አየር ኃይልና ሌሎች ኤጀንሲዎች ባደረጉት ትብብር የአደጋ ሰለባዎችን ማውጣት ችለዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ከናሽናል ትራስፓርቴሽን ሴፍቲ ቦርድ(ኤንቲኤስቢ) የመጣ ዘጠኝ አባላት ያሉት ቡድን በአላስካ አንቾራጅ ደርሶ የግጭቱ ምክንያት ምን እንደሆነ ምርመራ እያደረገ ይገኛሉ።
የኤንቲኤስቢ ሊቀመንበር ጀኒፈር ሆመንዲ ዘጠኝ ተሳፋሪዎችን አንድ ፓይሌት አሳፍሮ የነበረው ሴስና ባለፈው ሀሙስ እለት ከአላስካ ተነስቶ ከአርከሰቲክ በስተደቡብ 100 ማይል እርቀት ላይ ወደምትገኘው ሆም እያመራ በነበረበት ወቅት ቤሪንግ ባህር ሲደርስ ካራዳር ውጭ መሆኑን ገልጸዋል።
ባለስልጣናት እንደገለጹት የአሜሪካ ባህር ጠረፍ የአውሮፕላኑን ስብርባሪ ማግኘት የቻሉት አርብ ምሽት ነው።
"ትልቁ ትኩረት ተጎጂዎችን የመፈለግ ተግባር ነበር። ከእዚያ ስብርባሪውን መፈለግ ነበር" ብለዋል ሆመንዲ ቅዳሜ ጠዋት በሰጡት መግለጫ።
አደጋውን "ልብ ሰባሪ" ሲሉ የገለጹት ኃላፊዋ "ይህ እንዴት ሊከሰት እንደቻለ ለማወቅ ያለእረፍት እንሰራለን" ብለዋል። ይህ አደጋ የተከሰተው በአሜሪካ የአየር ደህንነት ጉዳይ ከፍተኛ ጥያቄ እየቀረበበት ባለበት ወቅት ነው።
ኤንቲኤስቢ መርማሪዎች በቅርቡ የደረሱትን ሁለት ከባድ አደጋዎች በመመርመር ላይ ይገኛል።
የአሜሪካ ጦር ሄሊኮፕተር ብላክ ሀውክ ሄሊኮፕተር ከመንገደኞች አውሮፕላን ጋር ዋሽንግተን አቅራቢያ ተጋጭቶ 67 ሰዎች የሞቱበቶ አደጋ አንደኛው ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በፊላደልፊያ የጤና ሄሊኮፕተር ተጋጭቶ ሰባት ሰዎች የሞቱበት አደጋ ነው።