የሩሲያ ውጭ ገዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ከ10 ሰአታት ወይይት በኋላ ለሰብአዊ መብት ሲባል ስምምነት ላይ መደረሱን ገልጸዋል
የሩሲያ ውጭ ገዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ከ10 ሰአታት ወይይት በኋላ ለሰብአዊ መብት ሲባል ስምምነት ላይ መደረሱን ገልጸዋል
በአዘርባጃንና በአርመን ሀይሎች በሞስኮ ስምምነት ከተደረሰ በኋላ በናጋርኖ ካራባክስ ለበርካታ ቀናት ሲካሄድ የነበረው ጦርነት አስተማማኝ ባይሆንም እደንቆመ ተነግሯል፡፡
በስምምነቱ ሁለቱ ኃይሎች በጦርነቱ ወቅት የሞቱ ወታሮችንና ምርኮኞችን ለመቀያየር ተስማምተዋል፡፡ የተኩስ አቁም ስምምነቱ ለምን ያህል ጊዜ ሊቆይ እንደሚችል የታወቀ ነበር የለም ተብሏል፡፡ ስምምነቱ እስከተፈረመበት ጊዜ ድረስ በሁለቱም ወገን ጦርነቱ ቀጥሎ እንደነበረና ስምምነቱ በመጣስ እርስበእርሳ ሲካሰሱ ነበር፡፡
የሞስኮው የተኩስ አቁም ስምምነት በሁለቱ ሃይሎች መካከል ለመጀመሪያ ጊዜ የተካሄድ የዲፕሎማሲ ግንኙነት ነው፤ ጦርነቱ በፈረንጆቹ መስከረም 27 ከተጀመረ በኋላ በሁለቱም ወገን በመቶ የሚቆጠሩ ሰዎች ሞተዋል፡፡
ጦርነቱ የተነሳበት ቦታ በአዘርባጃን ስር ቢሆንም ብዙ አርመኖች የሚኖሩበትና በአርመኖች የሚተዳደር ነው፡፡
ድርድሩን ያመቻቹት የሩሲያ ውጭ ገዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ በሰጡት መግለጫ ከ10 ሰአታት ወይይት በኋላ ለሰብአዊ መብት ሲባል ስምምነት ላይ መደረሱን ገልጸዋል፡፡
የአለምአቀፉ የቀይ መስቀል ኮሜቴ ስምምነቱ እንዲደረስ እርዳታ አድርጓል፡፡
ላቭሮቭ የተኩስ አቁም ዝርዝር ጉዳይ አለመታየቱን ገልጸው አርመኒያና አዘርባጃን በዝርዝር ገዳዮች ላይ ስምምት መድረስ አለባቸው ብለዋል፡፡