ሳዑዲ አረቢያም በሀገሯ የሚገኙ የሊባኖስ አምባሳደር በ48 ሰዓታት ውስጥ ሀገሪቱን ለቀው እንዲወጡ አዛለች።
በባህሬን በሀገሯ የሚገኙት የሊባኖስ አምባሳደር በ48 ሰዓትት ውስጥ ሀገሪቱን ለቀው እንዲወጡ ትእዛዝ አስተላለፈች።
የባህሬን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ትናንት ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው፤ ውሳኔው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሊባኖስ ባለስልጣናት ባህሬንን ተበመለከት እየሰጡ ያሉ መግለጫዎችን እና አቋሞችን በመቃወም የመጣ ነው ብሏል።
የባህሬን መንግስት ያሳለፈው ውሳኔ በሀገሪቱ ውስጥ የሚኖሩ የሊባስ ዜጎችን የማይመለከት መሆኑንም ሚኒስቴሩ በመግለጫው አስታውቋል።
የባህሬን እምርጃ ሳዑዲ የወሰደችውን እርምጃ ተከትሎ የመጣ ሲሆን፤ ሳዑዲ አረቢያ በሀገሯ የሚገኙ የሊባኖስ አምባሳደር በ48 ሰዓታት ውስጥ ሀገሪቱን ለቀው እንዲወጡ ትእዛዝ በማስተላፍ፤ በሊባኖስ የሚገኙትን አምባሳደሯንም መጥራቷ ይታወሳል።
ሳዑዲ አረቢያ እርምጃውን የወሰደችው የሊባኖስ የኢንፎርሜሽን ሚኒስትር ሳዑዲ አረቡያ በየመን ጦርነት ውስጥ የነበራትን ሚና በመተቸት የሰጡትን መግለጫ ተከትሎ እንደሆነ ታውቋል።
በርካታ የገልፍ ሀገራም የሊባኖስ የኢንፎርሜሽን ሚኒስትር ጆርጅ ኮርዳሂ የሰጡትን መግለጫ ተከትሎ በሀገራቸው የሚገኙትን የሊባኖስ አምባሳደሮች ለማብራሪያ ጠርተው የነበረ ሲሆን፤ የሚኒስትሩን መግለጫ ውድቅ የሚያደርግ ደብዳቤም አስገብተዋል።
የተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች፣ የሳዑዲ አረቢያ፣ የኩዌት እና የባህሬን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ለየብቻው ባወጡት መግለጫም፤ የሊባኖስ የኢንፎርሜሽን ሚኒስትር ጆርጅ ኮርዳሂ ዩኤኢ እና ሳዑዲ አረቢያ የመንን ለመደገፍ እና ሽብርተኛውን የሀውቲ ሚሊሻ ለመከላከል የሰሩትን ስራ በማናናቅ የሰጡትን መግለጫ ተቃውመዋል።