ባህሬን ከእስራኤል ጋር ግንኙቷን በማደስ 4ኛዋ የአረብ ሀገር ሆነች
ጠቅላይ ሚኒስትር ኒታኒያሁ የባህሬን ውሳኔ አዲስ የሰላም ምእራፍ ይከፍታል ብለውታል
አሜሪካ የመካከለኛው ምስራቋ ባህሬን ከእስራል ጋር ግንኙነቷን ማደሷን አስታወቀች
አሜሪካ የመካከለኛው ምስራቋ ባህሬን ከእስራል ጋር ግንኙነቷን ማደሷን አስታወቀች
ባህሬን ከግብጽ ከጆርዳን፤ከዩኤኢ በመቀጠል ግንኑቷን ከእስራኤል ጋር በማደስ አራተኛው የአረብ ሀገር መሆን ችላለች፡፡
በአንድ ወር ገዜ ውስጥ የመካከለኛው ምስራቅ ሀገር የሆነችው ባህሬን ከተባበሩት አረብ ኤምሬትስ በመቀጠል ከእስራኤል ጋር ግንኙነቷን ማደሷን አስታውቃለች፡፡ የባህሬን ውሳኔ ከእስራኤል ጋር በተራዘመ ግጭት ውስጥ የምትገኘውን ፍልስጤምን ይጎዳታል ተብሏል፡፡
የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ በትዊተር ገጻቸው እንዳስታወቁት ከባህሬኑ ንጉስ ሀሚድ ቢን አል ከሊፋ እና ከእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃን ኒታንያሁ ጋር በስልክ ተነጋግረዋል፡፡
ይህ ታሪካዊ ቀን ነው ያሉት ፕሬዘዳንቱ የሁለቱ ሀገራት መሪዎችም ይህን እንደሚደግሙት አምናለሁ ብለዋል፡፡
አሜሪካ፣ባህሬንና እስራኤል ባወጡት የጋራ መግለጫ የበለጸገ ኢኮኖሚ ባላቸው ሁለቱ ሀገራት መካከል ቀጥተኛ የሆነ ንግግር መከፈቱ በመካከለኛው ምስራቅ ለውጥ ለማምጣትና መረጋጋትን፣ጸጥታንና ብልጽግናን ለመጨመር እንደሚረዳ ገልጸዋል፡፡
ፍልስጤም በባህሬን ውሳኔ ቅር ተሰኝታለች፤ምክንያቷ ደግሞ እስራኤል በወረራ ከያዘችው የፍልስጤም ግዛት ትውጣ የሚለውን የረጅም ጊዜ የአረብ ሀገራት አቋምን ያዳክማል ብላ በመስጋቷ ነው፡፡
በአሜሪካ መንግስት አመቻችነት ዩኤኢና እስራኤል ከአንድ ወር በፊት ነበር ግንኙነታቸውን ያደሱት፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ኒታኒያሁ የባህሬን ውሳኔ አዲስ የሰላም ምእራፍ ነው ብለውታል፡፡