ብልጽግና ፓርቲ የምርጫውን ሂደት መገምገሙንና ምርጫው ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ ሆኖ መጠናቀቁን አስታውቋል
ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) ባወጣው መግለጫ 6ኛው ሀገርአቀፍ ምርጫ“ነፃ፣ፍትሃዊ እና ዴሞክራሲያዊ አልነበረም” ብሎ ለመደምደም የሚያስችሉ ተግባራት መፈጸማቸውን አስታውቋል፡፡
ፓርቲው ከምርጫ ዋዜማ ጀምሮ የታጠቁ የፖሊስና የመከላከያ አባላት ጦር መሳሪያ ይዘው በመረጩ ህዝብ ላይ የስነልቦና ጫና መፍጠና ሌሎች ችግሮች በቅድመ ምርጫ ወቅት መከሰታቸውን ገልጿል፡፡
እስካሁን ደረስኩበት ባለው ማጣራት በምርጫ እለትም በርካታ ችግሮችን ማስተዋሉን ፓርቲው በመግለጫው ጠቅሷል፡፡
“…ገዥው ፓርቲ እንዲመረጥ የሚደረዳ ገለጻ ማድረግ፣ ያልነበሩ አዳዲስ ምርጫ ጣቢያዎችን መክፈት፣አቅመ ደካሞችና በእድሜ የገፉ ሰዎችን በማገዝ ስም የሚገልጉትን ማስመረጥናባልደራስ የተመረጠባቸውን ወረቀቶች በስልት” ማድረግ ፓርቲው በድምጽ አሰጣጡ ወቅት አስተዋልኳቸው ካላቸው ችግሮች መካከል ናቸው፡፡
ፓርቲው በምርጫው እለት የፈጠሩት ረጃጅም ሰልፎች መረጮች ተሰላችተው እንዳይመርጡ የተደረገ ተግባር ነው ብሏል፡፡
መንግስትን የሚመራው ፓርቲ (ብልጽግና) በበኩሉ የምርጫውን ሂደት መገምገሙንና ምርጫው ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ ሆኖ መጠናቁቀን አስታውቋል፡፡
ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ 6ኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ በአብዛኛው በሰላም መጠናቀቁን አስታውቋል፡፡ ቦርዱ ከፓርቲዎች በርካታ ቅሬታዎች እየደረሰ መሆኑንና በምርጫ ውጤቱ ላይ ተጽእኖ ያሳድራሉ ባላቸው ቅሬታዎች ላይ ምርመራ እንደሚያካሂድ ማስታወቁ ይታወሳል፡፡