ምርጫ ቦርድ ፍርድ ቤቱ የባልደራስ እጩዎችን አስመልክቶ ያሳለፈውን ውሳኔ ለመፈጸም እቸገራለሁ አለ
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ግንቦት 13 2013 ዓ.ም ነው የባልደራስ እጩዎች እንዲመዘገቡ የወሰነው
የእጩዎች ምዝገባ የካቲት 30 ቀን 2013 ዓ.ም መጠናቀቁን ምርጫ ቦርድ አስታውቋል
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ በእስር ላይ የሚገኙ የባልደራስ አባላት ኢንዲመዘገቡ ያሳለፈውን ውሳኔ ለመፈጸም እንደሚቸገር አስታወቀ።
ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ባወጣው መግለጫ ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ በህግ ጥላ ስር ያሉ የፓርቲው እጩዎች የሆኑት አባላቱ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ግንቦት 13 2013 ዓ.ም ባሳለፈው የፍርድ ውሳኔ መሰረት እንዲመዘገቡ ማዘዙን አስታውቋል።
እንዲሁም ቦርዱ እስከ ግንቦት 19 2013 ዓ.ም ድረስ ተገቢውን ትእዛዝ ለምርጫ ወረዳዎች አስተላፎ እንደ ፍርዱ እንዲፈጸም ጥያቅ ማቅቡንም ገልጿል።
የእጩዎች ምዝገባ የካቲት 30 ቀን 2013 ዓ.ም መጠናቀቁን ያስታወሰው ቦርዱ፤ እያንዳንዳቸው የዕጩ ተወዳዳሪዎች በድምጽ መስጫ ወረቀት ላይ የሚኖራቸውን ስፍራ የሚወስን ሎተሪ እጣ በማውጣትና የድምጽ መስጫ ወረቀቶች ህትመትም ተጠናቆ ወደ ምርጫ ጣቢያ የመላክ ተግባር በቅርብ ጊዜ የሚጀመር መሆኑን አስታውቋል።
በዚህም መሰረት በህግ ጥላ ስር ያሉ የፓርቲው እጩዎችን አስመልክቶ እንደ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ ለመፈጸም የሚቸገር መሆኑንም ቦርዱ አስታውቋል።
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ባሳለፍነው ሰኞ ግንቦት 16 2013 በዋለው ችሎት የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ አመራሮች እስክንድር ነጋ፣ ስንታየሁ ቸኮል፣ ቀለብ ስዩም እና አስካለ ደመሌ ለፓርቲው በእጩነት ተመዝግበው መወዳደር እንደሚችሉ ውሳኔ መስጠቱ ይታወሳል።
የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ አመራሮች ባሳለፍነው ዓመት ሰኔ 2012 ዓ.ም የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳን ተከትሎ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ይታወሳል።