የባሌ ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ የዓለም ቅርስ ሆኖ በዩኔስኮ ተመዘገበ
የባሌ ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ በዩኔስኮ 11ኛው የኢትዮጵያ ቅርስ ሆኖ ተመዝግቧል
በትናንትናው ዕለት የጌድኦ ባህላዊ መልክአ-ምድር በዓለም ቅርስነት መመዝገቡ ይታወሳል
የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ በተባባሩት መንግስታት የትምህርት የሳይንስና እና የባህል ድርጅት /ዩኔስኮ/ በዓለም ቅርስነት ተመዘገበ፡፡
የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅትወይም ዩኔስኮ 45ኛ ጉባኤውን በሳውዲ አረቢያ ሪያድ እያካሄደ ይገኛል።
ኢትዮጵያ በሪያድ እየተካሄደ ባለው የዩኔስኮ ጉባኤ ላይ የቱሪዝም ሚኒስትሯ ናሲሴ ጫሊ፣ የኢትዮጵያ ቅርስ ጥናት ዳይሬክተር አበባው አያሌው እና ሌሎች ባለሙያዎች ተወክላለች።
ዩኔስኮ ሪያድ የዓለም ቅርስ ባዔው በኦሮሚያ ክልል የሚገኘውን የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ የዓለም ቅርስ ሆኖ መመዝገቡ ተገልጻል።
ዩኔስኮ በድረገጹ እንዳስታወቀው የባሌ ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ 11ኛው ቅርስ ሆኖ መመዝገቡን ለዓለም አብስሯል።
የባሌ ተራራዎች ብሔራዊ ፓርክ የተመዘገበው በኢትዮጰያ ሁለተኛው ታላቅ የተፈጥሮ ቅርስ ሆኖ ሲሆን በዓለም ደግሞ 11ኛው ቅርስ በመሆን ነው የተመዘገበው።
የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅትወይም ዩኔስኮ በትናንትናው ዕለት የጌድኦ ባህላዊ መልክአ-ምድር በዓለም ቅርስነት መመዝገቡ ይታወሳል።
በዓለም ቅርስነት የተመዘገበው የጌድኦ ባህላዊ መልከዓ ምድር በዕጽዋዕት፣ ፍራፍሬ እና በሰብል ምርቶች ታዋቂነትን ያተረፈ እንደሆነ ተገልጿል።
እንዲሁም መልክዓ ምድሩ ህብረተሰቡ ሀገር በቀል ዕውቀት ተጠቅሞ የአየር ሚዛን የተስተካከለ እንዲሆን በማስቻል እንዲሁም የመሬት አጠባበቅ እና አያያዝ ልምዱ ለሌሎች ህዝቦች ልዩ ተሞክሮና ልምድ የሚሰጥ ነውም ተብሏል።
ከዚህ በተጨማሪም የዚህ መልክዓ ምድር አንድ አካል የሆነው ይህ የዓለም ቅርስ በውስጡ የትክል ድንጋይ መካነ ቅርስንም ይዟል።
በዓለም ቅርስነት የተመዘገበው የጌድኦ ባህላዊ መልክዓ ምድር በውስጡ ከ6 ሺህ በላይ ትክል ድንጋዮችን የያዘ ሲሆን ተጨማሪ ጎብኚዎችን ለኢትዮጵያ እንደሚያስገኝ ይጠበቃል።