ዩኔስኮ በቻይና፣ በሕንድ፣ በኢራን እና በስፔን የሚገኙ ሥፍራዎች በዓለም ቅርስነት መዘገበ
የቻይናዋ ኩዋንዙ ከተማ በዩኔስኮ የዓለም ቅርስነት መመዝገብ ከቻሉ ስፍራዎች አንዷ ናት
እሰካሁን በዩኔስኮ የዓለም ቅርስ የተመዘገቡ ስፍራዎች ብዛት 56 መድረሱ መረጃዎች ያመላክታሉ
የተባበሩት መንግስታት የትምህርት ፣ የሳይንስ እና የባህል ድርጅት /ዩኔስኮ/ በቻይና ፣ በሕንድ ፣ በኢራን እና በስፔን የሚገኙ የባህል ሥፍራዎችን በዓለም ቅርስነት መዘገበ።
በየኔስኮ የተመዘገቡት ባህላዊ ስፍራዎቹ ከ10ኛ - 14ኛው ክፍለ ዘመን በነበሩ ጊዜያት የቻይናዋ ኩዋንዙ ከተማ ንዝረትና የገበያ ስህበት ሆኖ ሲያገለግል የነበረው የኩዋንዙ ስፍራ አንዱ ነው።
የህንዱ ካካቲያ ሩድሬሽዋራ (ራማፓ) ቤተ መቅደስ፣ የኢራን የባቡር መስመር እና የስፔን ፓሶ ዴል ፕራዶ እና ቡኤን ሬይሮ ፣ የጥበብና ሳይንስ መልከአ ምድርም በዩኔስኮ በቅርስነት ከተመዘገቡት ውስጥ ይገኛሉ።
የምስራቅ ቻይና የወደብ ከተማዋ ኩዋንዙ በአንድ ወቅት በጣልያናዊው አሳሽ ማርኮ ፖሎ “እጅግ ታላቅ እና የከበረች ከተማ” ተብላ የተወደሰችው ናት።
ኩዋንዙ በጥንታዊቷ ቻይናውያን የሶንግ ሥርወ መንግሥት (960-1279) እና በዩአን ሥርወ መንግሥት (1271-1368) ከታላላቅ ወደቦች መካከል አንዷም ነበረች።
የኩዋንዙ በዩኔስኮ መዝገብ የዓለም ቅርስ ስፍራዎች ብዛት ወደ 56 ከፍ እንዲል አድርጎታል፡፡
ሌላው በየኒስኮ የተመዘገበው በአሸዋ ድንጋይ የተገነባው የህንዱ ሺቫ ቤተመቅደስ ሲሆን፤ ግንባታው እንደፈረንጆቹ በ1213 መጀመሩንና ለ40 ዓመታት ያህል እንደቀጠለ ይታመናል።
ቤተ መቅደሱ ከፍተኛ ስነ-ጥበባዊ ጥራት ያላቸው ቅርፃ ቅርጾች፣ የክልል የዳንስ ልምዶችን እና የካካቲያን ባህልን የሚያሳዩ የጥበብ ውጤቶችም አሉት።
የ1 ሺህ 394 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው የኢራን የባቡር መስመር በሰሜን ምስራቅ ያለውን ካስፔያን ባሕርን በደቡብ ምዕራብ በኩል ከፐርሺያ ባሕረ ሰላጤ ጋር የሚያገናኝ ሲሆን ሁለት የተራራ ሰንሰለቶችን እንዲሁም ወንዞችን፣ ደጋማ ቦታዎችን፣ ደኖችን እና ሜዳዎችን እንዲሁም አራት የተለያዩ የአየር ንብረት ቦታዎችን የሚያቋርጥ ነው።
የባቡር ሀዲዱ እንደፈረንጆቹ በ1927 ተጀምሮ በ1938 የተጠናቀቀ ነው።
አራተኛው በዩኔስኮ በቅርስነት የተመዘገበው ፓስዮ ዴል ፕራዶ እና ቡን ሬትሮ የ 200 ሄክታር ስፋት ያለው ሲሆንየ፤ ቅርሱ በማድሪድ የከተማ እምብርት ነው የሚገኘው።