በ24 ሰዓታት ውስጥ በሙንባይ አካባቢ ብቻ 11 ተመሳሳይ የህንጻ መደርመስ አደጋዎች ደርሰዋል
በህንድ ሙንባይ በደረሰ የመሬት መንሸራተት አደጋ በትንሹ የ30 ሰዎች ህይወት ማለፉን የአካባው ባለስልጣናት አስታወቁ።
የመሬት መንሸራተት አደጋው በአካባው የጣለውን ከባድ ዝናብ ተከትሎ የደረሰ መሆኑንም ሮይተርስ ዘግቧል።
አደጋውን ተከትሎም በርካታ ቤቶች የተደረመሱ ሲሆን፤ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞችም የተረፉ ሰዎችን በማፈላለግ ላይ መሆናቸው ተነግሯል።
በፍርስራሹ ስር ሆነው የሚጮሁ ሰዎች ድምጽ መሰማቱን እና የአደጋ ጊዜ ሰራተኞችም የተጎዱ ሰዎችን ከህንጻዎች ፍርስራሽ ስር ሲያወጡም ተስተውሏል።
እንደ ህንድ ባለስልጣናት ገለጻ በ24 ሰዓታት ውስጥ በሙንባይ አካባ ብቻ 11 ተመሳሳይ ሆኑ ህንጻዎች መደርመስ አደጋዎች ደርሰዋል።
ለ24 ሰዓታት የጣለውን ከባድ ዝናብ ተከትሎም በሙንባይ ከተማ ሌሎች አካባዎች በጎርፍ መጥለቅለቃቸውም ነው የተነገረው።
ይህንን ተከትሎም በህንድ የንግድ ከተማ በሆነችው ሙንባይ የባቡር ትራንስፖርት አገልግሎትን ጨምሮ ልሎች አገልግሎቶች መስተጓጎላቻውም ታውቋል።
የማሃራሽታ ግዛቷ ሙንባይ በቀጣ 4 ቀናትም ከባድ ዝናብ እንደምታስተናግድ የሀገሪቱ ሜትሪዮሎጂ ኤጀንሲ አስታውቋል።
የህንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በበኩላቸው በአደጋው የደረሰው ጉዳት እንዳሳዘናቸው ገልጸው፤ ለተጎጂዎች አስፈላጊው ድጋፍ እንደሚደረግላቸው አስታውቀዋል።