ፕሬዝዳንት ዮሪ ሙሴቪኒ ምዝበራው እንዲመረመር አዘዋል
የዩጋንዳ ማዕከላዊ ባንክ በጠላፊዎች 17 ሚሊዮን ዶላር ተመዘበረ፡፡
ምስራቅ አፍሪካዊቷ ዩጋንዳ በማዕከላዊ ባንኳ ላይ በተፈጸመ ጥቃት 62 ቢሊዮን ሽልንግ ወይም 17 ሚሊዮን ዶላር ተዘርፋለች፡፡
እንደ ሀገሪቱ ቢው ቪዥን ጋዜጣ ዘገባ ከሆነ ምዝበራው የተፈጸመው ጠላፊዎች የባንኩን አይቲ ክፍል ከተቆጣጠሩ በኋላ ነው፡፡
ባሳለፍነው ማክሰኞ ተፈጽሟል በተባለው ይህን ምዝበራ በደቡብ እስያ የሚገኙ ጠላፊዎች የተፈጸመ ሲሆን ገንዘቡ በመጨረሻም ወደ ጃፓን እንደተላከ ባንኩ አስታውቋል፡፡
ባንኩ እንዳስታወቀው ከተመዘበረው ገንዘብ ውስጥ ግማሹን አስመልሻለሁ ብሏል፡፡
አሜሪካ ለራሷ የተጋነነ ግምት እንዳላት የኡጋንዳ ፕሬዝዳንት ተናገሩ
የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ዮሪ ሙሴቪኒ መንግስታቸው በሚስተዳድረው ባንክ ላይ የተፈጸመው ምዝበራ እንዲመረመር አዘዋል ተብሏል፡፡
ዘግይቶ በወጣው ዘገባ መሰረት ይህ ምዝበራ የተፈጸመው በባንኩ የውስጥ ሰራተኞች እርዳታ አማካኝነት ሳይሆን እንደማይቀር ዴይሊ ሞኒተር ዘግቧል፡፡
የፕሬዝዳንቱን ጥዕዛዝ ተከትሎ ፖሊስ ሁኔታውን እየመረመረ ነው የተባለ ሲሆን በቅርቡ ውጤቱን ለህዝብ ይፋ እንደሚያደርግ ገልጿል፡፡
ዩጋንዳ በተደጋጋሚ መሰል የበይነ መረብ ጥቆቶችን ስታስተናግድ የአሁኑ የመጀሪያዋ ሳይሆን በተለይም በቴሌኮም ኩባንያዎች እና የገንዘብ አስተላላፊ ተቋማቶቿ ላይ በተደጋጋሚ ተፈጽሟል፡፡
ይሁንና በባንኮች ላይ መሰል ምዝበራዎች የሚፈጸሙ ቢሆንም ባንኮች ከደንበኞቻቸው ሊደርስ የሚችልን ጉዳት በመፍራት ምን ያህል ገንዘብ እንደተሰረቁ ከመናገር ይቆጠባሉ፡፡