የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ እና ሚሼል ኦባማ ትዳር ፈርሶ ይሆን?
ሚሼል ኦባማ ባሳለፍነው ሳምንት በተካሄደው የቀድሞ ፕሬዝዳንት የጅሚ ካርተር ስርዓተ ቀብር ላይ አልታዩም
በዶናልድ ትራምፕ በዓለ ሲመት ላይ አይገኙም የተባሉት ሚሼል ኦባማ ከባለቤታቸው ባራክ ኦባማ ጋር ተለያይተዋል እየተባለ ይገኛል
የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ እና ሚሼል ኦባማ ትዳር ፈርሶ ይሆን?
ዲሞክራቶቹ የቀድሞው ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ እና ባለቤታቸው ሚሼል ትዳር ንፋስ ገብቶታል የሚሉ አስተያየቶች በስፋት እየተሰራጩ ይገኛል።
ይህ ዜና በስፋት መወራት የጀመረው ደግሞ የቀድሞ ቀዳማዊ እመቤት ሚሼል ኦባማ ከባለቤታቸው ጋር በአደባባዮች እየታዩ አይደለም በሚል ነው።
ሚሼል ኦባማ ባሳለፍነው ሳምንት ስርዓተ ቀብራቸው በተፈጸመው የቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጅሚ ካርተር የስንብት ፕሮግራም ላይ አልታዩም።
እንዲሁም ከቀናት በኋላ በሚካሄደው የተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በዓለ ሲመት ላይ እንደማይገኙም ሚሼል ኦባማ አሳውቀዋል።
ይህን ተከትሎም በአሜሪካ ፖለቲካ ላይ ተጽዕኖ ያላቸው ሁለቱ ባልና ሚስቶች ትዳር ወደ ፍቺ እያመራ ነው በሚል ዴይሊ ሜይል ዘግቧል።
እንደ ዘገባው ከሆነ የሁለት ሴት ልጆች ወላጅ የሆኑት ኦባማ እና ሚሼል በቅርቡ በአደባባይ መፋታታቸውን ሊያውጁ እንደሚችሉ ተገልጿል።
ባልና ሚስቶቹ ትዳራቸው ነፋስ ገብቶታል ሲባል የአሁኑ የመጀመሪያው ሳይሆን በቀድሞ የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ኔልሰን ማንዴላ ስርዓተ ቀብር ላይ ባራክ ኦባማ የዴንማርኳን ጠቅላይ ሚንስትር ሰውነት ተመስጦ ሲመለከት የሚያሳይ ምስል ከተሰራጨ በኋላም ሊፋቱ እንደሚችሉ ተገልጾ ነበር።
እንዲሁም ባልና ሚስቶቹ በነጩ ቤተ መንግሥት ውስጥ በሚኖሩበት ወቅት አልጋ እንደለዩ ሲዘገብም ነበር።
ባራክ ኦባማ ትኩረቱን በግል ህይወታቸው ዙሪያ ያዱረገው እና በ2013 ባሳተሙት መጽሀፋቸው ላይ ትዳራቸው በተደጋጋሚ ፈተና ገጥሞት እንደነበር ጠቅሰዋል።
ይህ በዚህ እንዳለም ሚሼል ኦባማ ከባላቸው ባራክ ኦባማ ጋር በአደባባዮች ያልታዩት ትዳራቸውን ለመፍታት በመወሰናቸው ሳይሆን በቅርቡ እናቷን በሞት ስላጣች እና ሀዘን ላይ በመሆኗ ነውም ተብሏል።