ባርሴሎና ከኩባንያው ጋር ቴክኒካዊ ማማከር ለማግኘት ክፍያ መፈጸሙን አምኗል
ባርሴሎና እግር ኳስ ክለብ ለቀድሞው የስፔን የዳኞች ኮሚቴ ምክትል ፕሬዝዳንት ለሆሴ ማሪያ ኤንሪኬዝ ኔግሬራ በከፈለው ክፍያ የሙስና ክስ ቀርቦበታል።
የስፔኑ ክለብ ባርሴሎና ከፈረንጆቹ 2001 እስከ 2018 ባለው ጊዜ ውስጥ 8 ነጥብ 4 ሚሊየን ዩሮ ለኔግሬራ መክፈሉ ባለፈው ወር ተገልጿል።
በዚህም የባርሴሎና የቀድሞ የክለቡ ባለስልጣናት እና ኔግሬራ "በሙስና፣ "እምነትን በመጣስ እና በሀሰት የንግድ ሰነድ" ከስ ተመስርቶባቸው ፍርድ
ክሶች ክለቡን እንዲሁም የቀድሞ ፕሬዝዳንቶች፤ ጆሴፕ ማሪያ ባርቶሚ እና ሳንድሮ ሮሴልን ላይ ያነጣጠሩ ናቸው ተብሏል።
ባርሴሎና ከጆሴ ማሪያ ኤንሪኬዝ ኔግሬራ ጋር በጥብቅ ሚስጥራዊ የሆነ የቃል ስምምነትን ገንዘብ በመክፈል ክለቡን የሚጠቅም እርምጃዎችን እንደወሰዱ አስደርጓል የሚል እንደሆነ ዐቃቤ ህግ ተናግሯል።
ባለፈው ወር የግብር ባለስልጣናት በኔግሬራ ኩባንያ ዳስኒል 95 ላይ ባደረገው ምርመራ ነው ክፍያው መፈጸሙ ይፋ የሆነው።
ባርሴሎና የእግር ኳስ ክለብ ለዳስኒል 95 ክፍያ እንደከፈለው አምኗል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።
ክለቡ ከኩባንያው ጋር ቴክኒካዊ ማማከር ለማግኘት ኮንትራት መግባቱን ገልጾ፤ "በፕሮፌሽናል ክለቦች ዘንድ የተለመደ ተግባር ነው" ሲልም አክሏል።
ከ20 የስፔን ላሊጋ ክለቦች 18ቱ በጉዳዩ ላይ "አሳስቦናል" የሚል መግለጫ መስጠታቸውን ተከትሎ ውጥረት ነግሷል።