ልዩልዩ
የጃፓን ደጋፊዎች ሀገራቸው ስፔንን ብታሸንፍም ደስታቸውን ያዝ አድርገው ስታዲየም አጽድተዋል
ጃፓን በትናትናው እለት ሰፔንን 2ለ1 አሸንፋ ወደ ጥሎ ማለፍ ገብታለች
ጃፓን በዓለም ዋንጫው የ 2010 እና 2014 የዓለም ዋንጫ አሸናፊዎች መርታት ችላለች
በኳታር የዓለም ዋንጫ ጃፓን 2010 እና 2014 የዓለም ዋንጫ አሸናፊዎች መርታት ምድብ አምስትን በበላይነት እየመራች ወደ ቀጣይ ዙር ማለፍ ችላለች።
በተለይም በትናትናው እለት ጃፓን ከስፔን ጋር ያደረገችውን ጨዋታ 2ለ1 በማሸነፍ ወደ ጥሎ ማለፍ መቀላቀል መቻሏ ጃፓናውያን ዘንድ ከፍተኛ ደስታን ፈጥሯል።
በኳታር ተገኝተው ጨዋታውን ሲከታተሉ የነበሩ የጃፓን ደጋፊዎችም ደስታቸውን በተለያየ መንገድ ሲገልጹ ቢቆዩም የዘወትር ተግባራቸውን ከመፈጸም ግን አልቦዘኑም።
በደስታ ውስጥ የነበሩት የጃፓን ደጋፊዎች ጨዋታው ከለቀ በሁዋላ ስታዲየሙን ሲያጸዱ መታየታቸው በርካቶች ዘንድ ግርምትን ፈጥሯል።
የጃፓን ብሄራዊ ቡድን ደጋፊዎች ከዚህ ቀደምም ሀገራቸው ጀርመንን በረታችበት ጨዋታ ላይ ጨዋታው ከተጠናቀቀ በሁዋላ ስታዲየም ሲያጸዱ መታየታቸው አይዘነጋም።
የምድብ አምስት የመጨረሻ ጨዋታዎች ጃፓን የዓለም ዋንጫ በሪትሱ ዶአን እና ኣኦ ታናካ ጎሎች አሸናፊዋን ስፔን 2ለ1 በሆነ ውጤት በመርታት ወደ ጥሎ ማለፍ መግባቱዋ ይታወሳል።
ምድብ አምስትን በበላይነት ያጠናቀቀችው ጃፓን በጥሎ ማለፉ በቀጣይ ከክሮሺያ ጋር የፊታችን ሰኞ የምትጫወት ይሆናል።