ጋብቻ ከመመስረትዎ በፊት ሊያስቡባቸው የሚገቡ ጉዳዮች ምን ምን ናቸው?
በዓለማችን በየዕለቱ 115 ሺህ ሰዎች ጋብቻ ይፈጸማሉ
ኮሮና ቫይረስ የተከሰተበት 2021 ዓመት በታሪክ ዝቅተኛ ጋብቻ የተፈጸመበት ዓመት ሆኖ አልፏል
ጋብቻ ከመመስረትዎ በፊት ሊያስቡባቸው የሚገቡ ጉዳዮች ምን ምን ናቸው?
ከሰው ልጆች የህይወት ምርጫዎች መካከል አንዱ የሆነው ጋብቻ ወይም ትዳር በባልና ሚስት ፈቃድ አማካኝነት የሚመሰረት ነው፡፡
የማህበረሰብ ጠንካራ መሰረት እንደሆነ የሚነገርለት ትዳር ወይም ጋብቻ ሰዎች ለዚህ ውሳኔ ሲደርሱ የተለያዩ ጉዳዮችን ከግምት ውስጥ ያስገባሉ፡፡
የጋብቻ መስፈርቶች እንደ ሰዎች ምርጫ እና ፍላጎት የተለያዩ ቢሆኑም የስነ ልቦና ባለሙያዎች ከማግባትዎ በፊት ቢነጋገሩባቸው ቢሉ የሚከተሉትን ምክረ ሀሳቦች አስቀምጠዋል፡፡
መቀመጫውን በአሜሪካ ኒዮርክ ከተማ ባደረገው ኒዮርክ ኤስሊ ቶክ ባደረገው የጋብቻ አማካሪ ተቋም ውስጥ ባለሙያ የሆኑት ላንዲስ ቢጃር ጋብቻ ዘላቂ እና ውጤታማ እንዲሆን አምስት ዋና ዋና ጉዳዮችን አስቀምጠዋል፡፡
እንደ ባለሙያዋ ማብራሪያ ከሆነ ለስኬታማ ትዳር የመጀመሪያው ነገር ስለ ህጻናት ማውራት አስፈላጊ ነው ያሉ ሲሆን ከዚህ ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ዙሪያ የጋራ እና ተመሳሳይ አመለካከት መኖሩን ማረጋገጥ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
ፍቅረኛሞች ከመጋባታቸው በፊት ልጅ ስለመውደዳቸው፣ እንክብካቤዎችን ስለማድረግ፣ ሊወልዷቸው ስላሰቧቸው ልጆች ብዛት እና ሌሎችም ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ በግልጽ ተመሳሳይ አቋም መያዝ አለባቸውም ብለዋል፡፡
ሌላኛው ጥንዶች ከመጋባታቸው በፊት ሊያስቡባቸው የሚገባው ጉዳይ የገንዘብ አቅም ሲሆን በዚህ ጉዳይ ዙሪያ በግልጽ ማውራት ከተጋቡ በኋላ ሊከሰቱ የሚችሉ ችግሮችን ለመፍታት እና ትዳሩን ለማስቀጠል ይጠቅማቸዋል ተብሏል፡፡
አንድ ሰው ስለ ገንዘብ ያለው አመለካከት በህይወቱ ላይ ትልቅ አስተዋጽኦ ይኖረዋል የተባለ ሲሆን በተለይም በገንዘብ ምንጭ፣ አጠቃቀም እና ቀጣይ እቅዶች ዙሪያ በግልጽ መወያየት አስፈላጊ መሆኑን ባለሙያዋ ተናግራለች፡፡
የጥንዶቹ ቤተሰባዊ ህይወት ለትዳር ስኬት ላኛው ቁልፍ ጊዳይ ሲሆን ጥንዶች ከመጋባታቸው በፊት ስለ ቤተሰቦቻቸው ፍላጎት፣ አኗኗር ሁኔታ እና ባህል በሚገባ መተማመን ያስፈልጋል ተብሏል፡፡
ሌላኛው ጋብቻን የሚፈትነው ጉዳይ ዕምነት እና ባህል ሲሆን ሊጋቡ ያሰቡ ጥንዶች ስለ ዕምነታቸው እና ባህላቸው በሚገባ መተዋወቅ፣ መወያየት እና ጉዳዮቹ በትዳራቸው ላይ ሊያመጡ በሚችሉ አስተዋጽኦዎች ላይ መተማመን እንዲኖርም ባለሙዋ መክረዋል፡፡
በዓለማችን በየዕለቱ 115 ሺህ ጋቻዎች የሚመሰረቱ ሲሆን ከቅርብ ዓመት ወዲህ ደግሞ የጠጋቢዎች ቁጥር እየቀነሰ ሲመጣ የፈረንጆቹ 2021 ደግሞ በ50 ዓመት ታሪክ ዝቅተኛ ጋብቻ የተመሰረተበት ዓመት ሆኖ ተመዝግቧል፡፡