የቻይናው ዩኒቨርስቲ ለመጀመሪያ ጊዜ ከጋብቻ ጋር የተገናኘ የትምህርት አይነት አስተዋወቀ
የጋብቻ ምጣኔ እየቀነሰ ባለባት ሀገር እንዲህ አይነት መርሃግር እያስፈልግም ሲሉ በርካቶች ትችት ሰንዝረዋል
ቻይና በህንድ ከመለጧ በፊት በህዝብ ቁጥር ከአለም አንደኛ ደረጃን ይዛ ቆይታለች
የቻይናው ዩኒቨርስቲ ለመጀመሪያ ጊዜ ከጋብቻ ጋር የተገናኘ የትምህርት አይነት አስተዋወቀ።
የቻይና የማህበረሰብ ጉዳይ ዩኒቨርሲቲ ከጋብቻ ጋር ተዛማጅነት ያላቸውን ኢንዱስትሪዎችን እና ባህሎች ለማዳበር በማለም በመጀመሪያ ዲግሪ ደረጃ የጋብቻ መርሃግብር ይፋ አድርጓል።
የጋብቻ ምጣኔ እየቀነሰ ባለባት ሀገር እንዲህ አይነት መርሃግር እያስፈልግም ሲሉ በርካቶች ዌቦ በተባለው የቻይና ማህበራዊ ሚዲያ ትችት ሰንዝረዋል።
በመጭው መስከረም በሚጀመረው በዚህ መርሃግብር መቀመጫውን ቤጂንግ ያደረገው ተቋም "ከጋብቻ ጋር ግንኘነት ያላቸው ኢንዱስትሪዎችን እና ባህልን የሚያሳድጉ ባለሙያዎችን ለማፍራት"አልሟል።
የቻይና ህዝብ ቁጥር በፈረንጆች 2023 ለሁለት ተከታታይ አመታት መቀነሱን ተከትሎ የፖሊሲ አውጭዎች ከጋብቻ ምጥነት መቀነስ ጋር የተያያዘውን የውልደት መጠን ለመቀየር ጥረት እያደረጉ ናቸው። በቻይና ልጅ የሚወልዱ ጥንዶች ልጃቸውን አስመዝገበው ጥቅማጥቅም ይሰጣቸዋል።
'ሜሬጅ ሰርቪስስ እና ማኔጅመንት' የሚል ስያሜ የተሰጠው አዲሱ የዲግሪ መርሃግብር የቻይናን የጋብቻ ባህል በጎነት እና ቤተሰባዊ ባህልን የሚያጎሉ የጋብቻ ኢንዱሰትሪዎችን በማበልጸግ ላይ እንደሚያተኩር ሮይተርስ የቻይናውን ግሎባል ታይምስ ጠቅሶ ዘግቧል።
ዩኒቨርስቲው በዚህ አመት "በቤተሰብ ማማከር፣ በዘመናዊ የጋብቻ ስነስርአት አፈጻጸም እና በጥንዶች ማጣመር" ጨምሮ በሌሎች መስኮች የሚሰለጥኑ 70 ተማሪዎችን ከ12 ግዛቶች ይመዘግባል።
በቻይና ብዙ ወጣት ሰዎች ሳያገቡ መኖርን ይመርጣሉ፤ ወይም በስራ እድል ውስንነት ምክንያ ማግባት አይፈጉም።
ቻይና በህንድ ከመለጧ በፊት በህዝብ ቁጥር ከአለም አንደኛ ደረጃን ይዛ ቆይታለች። ሀገሪቱ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እያጋጠማት ያለው የወሊድ ምጣኔ መቀነስ ግን ስትከተለው የነበረውን 'የአንድ ህጻን' (ዋን ቻይልፖሊሲ) እንድትተወው አድርጓታል።