ቻይና የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር “የተሳሳተ መረጃ እያሰራጩ ነው” ስትል አወገዘች
ዋሸንግተን ቤጅንግን ለመጨቆንና ኃያልነቷን ለማስቀጠል የምታደረገውን ጥረት ተቃውማለች
ቻይና ከሩሲያ በበለጠ የአሜሪካ ስጋት እንደሆነች የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ተናግረው ነበር
ቻይና በፖሊሲዎቿ ላይ “የተሳሳተ መረጃ እያሰራጩ ነው” ስትል የአሜሪካን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከንን አወገዘች።
የቻይና ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት፤ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ቻይናን በተመለከተ የተሳሳ መረጃ ማሰራጨታቸውን ገልጿል።
አንቶኒ ብሊንከን፤ የቻይናን የውጭና የሀገር ውስጥ ፖሊሲዎች የተመለከተ የተሳሳተ መረጃ ማሰራጨታው ቻይናን አስቆጥቷል።
የቻይናን የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ቃል አቀባይ ዋንግ ዌንግ ቢን ለአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በሰጡት ምላሽ፤ ዋሸንግተን የቤጅንግን ልማት ለመጨቆን እና ሃያልነቷን ለማስቀጠል የምታደረገውን ጥረት በግልጽ እንደሚቃወሙ ገልጸዋል።
አሜሪካ የዓለም ኃያል እንደሆነች መቀጠል እንደምትፈልግ ገልጸዋል።
የአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ቻይና ከሩሲያ በላይ የሀገራቸው ስጋት እንደሆነች ገልጸው ነበር።
ለዓለም ስርዓት መቀየር ከሩሲያ በላይ ስጋት የምትሆነው ቻይና እንደሆነች ገልጸው የነበሩት ብሊንከን ለቻይና አጸፋዊ እርምጃ ሊሰጥ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
አሜሪካ አሁንም ኃያልነቷን ማስቀጠል እንደምትፈልግ ብሊንከን መናራቸው ተዘግቧል። ቻይና ደግሞ ስሟ አላግባብ መነሳቱን አውግዛለች።
ቻይና በትናትናው እለት “ለአሜሪካ ከባድ ማስጠንቀቂያ ነው” ያለችውን ወታደራዊ ልምምድ በታይዋን አቅራቢያ ማድረጓን የሀገሪቱ ጦር መግለጹ ይታወሳል።
የቻይና ጦር የምስራቃዊ እዝ በታይዋን ዙሪያ የውጊያ ዝግጁነት ልምምዶችን እና ሌሎች የስልጠናዎችን በባህር እና አየር ላይ ማካሄዱንም የወታደራዊ እዙ ቃል አቀባይ ኮሎኔል ሺ ዪ ተናግረዋል።
ልምምዱ አሜሪካ ለታይዋን እውቅና ለመስጠት እያደረገችው ላለው እንቅሰቃሴ “ከባድ ማስጠንቀቂያ” መሆኑንም ቃል አቀባዩ ገልፀዋል።