ቻይና “ለአሜሪካ ከባድ ማስጠንቀቂያ ነው” ያለችውን ወታደራዊ ልምምድ በታይዋን አቅራቢያ አደረገች
ቻይና በቅርቡ በታይዋን አቅራቢያ ጠንከር ያለ ወታደራዊ ልምምድ አድርጋለች
አሜሪካ፤ ታይዋንን ከቻይና ወረራ ለመጠበቅ ኃይል ልትጠቀም እንደምትችል አስታውቃለች
ቻይና “ለአሜሪካ ከባድ ማስጠንቀቂያ ነው” ያለችውን ወታደራዊ ልምምድ በታይዋን አቅራቢያ ማድረጓን የሀገሪቱ ጦር አስታውቋል።
የቻይና ጦር ቃል አቀባይ በትናትናው እለት እንዳስታወቀው፤ ቻይና እራሷን በራስ የምታስተዳድር ደሴት ላይ ያላትን ቁርጠኝነት ለአሜሪካ ለማሳየት በቅርቡ በታይዋን አቅራቢያ ተከታታይ ወታደራዊ ልምምዶችን አድርጋለች።
የቻይና ጦር የምስራቃዊ እዝ በታይዋን ዙሪያ የውጊያ ዝግጁነት ልምምዶችን እና ሌሎች የስልጠናዎችን በባህር እና አየር ላይ ማካሄዱንም የወታደራዊ እዙ ቃል አቀባይ ኮሎኔል ሺ ዪ ተናግረዋል።
ልምምዱ አሜሪካ ለታይዋን እውቅና ለመስጠት እያደረገችው ላለው እንቅሰቃሴ “ከባድ ማስጠንቀቂያ” መሆኑንም ቃል አቀባዩ ገልፀዋል።
ታይዋን የግዛቴ አንድ አካል ናት የምትለው ቻይና በታይዋን ጉዳይ ከአሜሪካ ጋር ጭምር በተደጋጋሚ ግጭት ውስጥ ስትገባ ይታያል።
ባሳለፍነው ሳምንት በእስያ ጉብኝት ያደረጉት የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ኀገራቸው ታይዋንን ለመጠበቅ ኃይል ልትጠቀም እንደምትችል መናገራቸው ይታወሳል።
ባይደን ቻይና ታይዋንን በተመለከተ ኃይል የምትጠቀም ከሆነ እኛም መጠቀማችን አይቀርም ብለዋል።
የቻይናው ፕሬዝዳንት ዢ ጅንፒንግ ከወራ በፊት ታይዋንን ከቻይና ጋር ለማዋሃድ መዛታቸው የሚታወስ ሲሆን፤ ፕሬዝዳንቱ ለማዋሃድ ኃይል መጠቀም ስለማሰባቸው አልተናገሩም።
ታይዋን ነጻ ሀገር ነኝ የምትል ሲሆን፤ በአንጻሩ ታይዋንን የግዛቷ አካል አድርጋ ትመለከታታለች።