ሩሲያ በዩክሬን ላይ እያካሄደች ያለውን ጦርነት የደገፈችው ቤላሩስ ከሩሲያ ጋር ወታደራዊ ትበብር አድርጋለች
ቤላሩስ በድንበር ላይ ከሩሲያ ጋር የጋራ ጦር መሰማራቱ የመከላከያ እርምጃ እንደሆነ ተናግራለች።
ቤላሩስ ማክሰኞ እንዳስታወቀችው ጦሯ በድንበሮቿ ላይ ከሚገኙት የሩሲያ ወታደሮች ጋር ማሰማራቷ ሊሰነዘርባት የሚችል ጥቃት ለመከላከል መሆኑን አስታውቃለች።
"በአሁኑ ጊዜ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት በሙሉ በድንበራችን አቅራቢያ ለሚደረጉ ድርጊቶች በቂ ምላሽ ለመስጠት ያለመ ነው" ሲል የመከላከያ ሚኒስቴር ገልጿል።
ፕሬዝዳንት አሌክሳንደር ሉካሼንኮ ኪየቭ እና ምዕራቡ ዓለም ደጋፊዎቿ ለቤላሩስ ግልፅ ስጋት ናቸው ብለዋል።
ፕሬዝደንቱ ለሚሰነዘር ጥቃት ምላሽ ለመስጠት ወታደሮች ከሩሲያ ጦር ጋር በዩክሬን አቅራቢያ እንዲሰማሩ ማዘዛቸውን ሰኞ እለት ተናግረዋል።
ሩሲያ በዩክሬን ላይ እያካሄደች ያለውን ጦርነት የደገፈችው ቤላሩስ ከሩሲያ ጋር ወታደራዊ ትበብር በማድረግ የሩሲያ ሀገር ነች።
ሩሲያም ለቤላሩስ ዘመናዊ የጦር መሳሪያዎችን ስታስታጥቅ መቆየቷ ይታወሳል።