ፖለቲካ
ቤላሩስ ከሩሲያ የኑክሌር መሳሪያ መቀበል መጀመሯን አስታወቀች
ፕሬዝደንቱ የተወሰኑት መሳሪያዎች አሜሪካ 1945 ሄሮሽማ እና ናጋሳኪ ላይ ከጣለችው ከአቶሚክ ቦንብ ሶስት እጥፍ አውዳሚ እንደሆኑ ተናግረዋል
"ከሩሲያ የተቀበልናቸው ሚሳይሎች እና ቦምቦች አሉን" ሲሉ ኘሬዝደንት ሉካሸንኮ ተናግረዋል
የቤላሩስ ፕሬደዝደንት አሌክሳንደር ሉካሸንኮ ቤላሩስ ከሩሲያ የታክቲካል ኑክሌር መሳሪያ መቀበል መጀመሯን አስታውቀዋል።
ፕሬዝደንቱ የተወሰኑት መሳሪያዎች አሜሪካ 1945 ሄሮሽማ እና ናጋሳኪ ላይ ከጣለችው ከአቶሚክ ቦንብ ሶስት እጥፍ አውዳሚ እንደሆኑ ተናግረዋል።
ሩሲያ ከሶቬት ህብረት መውደቅ በኋላ ጦርነት ላይ ሊውሉ የሚችሉ የአጭር ርቀት ኑክሌር መሳሪያ ወደ ውጭ ስትልክ የመጀመሪያዋ ነው።
"ከሩሲያ የተቀበልናቸው ሚሳይሎች እና ቦምቦች አሉን" ሲሉ ሉካሸንኮ ለሩሲያ ሚዲያ መናገራቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።
ፕሬዝዳንቱ መሳሪያዎቹ ከአቶሚክ ቦንብ ሶስት እጥፍ አውዳሚ የሆኑ እንደሚገኙበትም ገልጸዋል።
የሩሲያው ፕሬዝደንት ፑቲን ባለፈው አርብ እለት እንደተናገሩት ልዩ መቀመጫ ከተገነባ በኋላ በቤላሩስ የሚቀመጡት የኑክሌር መሳሪያዎች ሩሲያ እንደምትቆጣጠር መግለጻቸው ይታወሳል።
ፑቲን ባለፈው መጋቢት ነበር ኑክሌር ወደ ቤላሩስ እንደሚልኩ ይፋ ያደረጉት።
ቤላሩስ የሩሲያ ዋነኛ አጋር ስትሆን በሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት ጉዳይ ለሩሲያ ድጋፋን ገልጻች።