ዩክሬን ያለማቋረጥ ከቤላሩስ ሊደርስ የሚችልን ጥቃት ስታስጠነቅቅ ከርማለች
ሩሲያ እና ቤላሩስ ሰኞ ዕለት የጋራ ወታደራዊ ልምምድ የጀመሩ ሲሆን ይህም በኪቭ እና በምዕራቡ ዓለም ስጋትን ፈጥሯል።
ሞስኮ አጋሯን ተጠቅማ በዩክሬን ላይ አዲስ የምድር ጥቃት ልትከፍት ትችላለች የሚል ፍርሀት ነግሷል።
ሩሲያ ባለፈው የካቲት ወር በጀመረችው ጦርነት ጎረቤት ቤላሩስ እንደ መንደርደሪያ ተጠቅማለች ተብሏል።
ሁለቱ አጋሮች ከፈረንጆቹ ጥር 16 እስከ የካቲት አንድ ድረስ የአየር ኃይል ልምምዶችን እንደሚያካሂዱ ሮይተርስ ዘግቧል።
ሁሉንም የቤላሩስ ወታደራዊ አየር ማረፊያዎችን በመጠቀም እና "የሜካኒዝ ብርጌድ ንዑስ ክፍልን" ያካተተ የጋራ ወታደራዊ ልምምድ መጀመሩን የቤላሩስ መከላከያ ሚንስቴር አስታውቋል።
ቤላሩስ የአየር ልምምዱ "መከላከያ" ስለሆነ ወደ ጦርነቱ እንደምትገባ ተናግራለች።
የቤላሩስ የመከላከያ ሚኒስቴር በማህበራዊ ትስስር ገጹ የሀገሪቱ የጸጥታ ምክር ቤት ምክትል ጸሀፊ ፓቬል ሙራቬይኮ “እስካሁን በትዕግስት እየጠበቅን ነው፣ የጥይቶቻችንን ባሩድ ደረቅ እንዲሆን እናደርጋለን" ብለዋል።
ሙራቬይኮ በሀገሪቱ ደቡባዊ ድንበር ላይ ያለው ሁኔታ "በጣም የተረጋጋ አይደለም" ያሉ ሲሆን፤ ዩክሬን ቤላሩስን "እየጠነቆለች ነው" ብለዋል።
"በዩክሬን በኩል ለሚደረጉ ማናቸውም ቀስቃሽ ድርጊቶች ዝግጁ ነን" ሲሉም አክለዋል።
ሞስኮ የቤላሩስ ፕሬዝዳንት አሌክሳንደር ሉካሼንኮ በዩክሬን ግጭት ውስጥ የበለጠ ንቁ ሚና እንዲጫወቱ ግፊት እያደረገች ነው መባሏን አጣጥላለች።
ዩክሬን ያለማቋረጥ ከቤላሩስ ሊደርስ የሚችልን ጥቃት ስታስጠነቅቅ ከርማለች።
ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ ባለፈው ሳምንት ሀገሪቱ ከቤላሩስ ጋር በሚያዋስናት ድንበር ላይ ዝግጁ መሆን እንዳለባት ተናግረዋል፡