አቶ በለጠ ሞላ አዲሱ የአብን ሊቀመንበር ሆነው በፓርቲው ተሰይመዋል
አቶ በለጠ ሞላ አዲሱ የአብን ሊቀመንበር ሆነው በፓርቲው ተሰይመዋል
የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ከሰሞኑ ባካሄደው አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ አቶ በለጠ ሞላን የንቅናቄው ሊቀመንበር አድርጎ መርጧል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም፡-
የቀድሞው የንቅናቄው ሊቀመንበር ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ፣ አብን የአማራን ሕዝብ ጥያቄ መመለሥ በሚያስችለውና ወቅቱ በሚፈልገው ልክ ይገኝ ዘንድ ላለፉት ጊዜያት የመጣበትን መንገድ መርምሮ በጥናት ላይ የተመሰረተ መዋቅራዊ ማሻሽያ መዘጋጀቱን መግለጻቸውንም ንቅናቄው ይፋ አድርጓል፡፡
ጠቅላላ ጉባዔው 5 ተለዋጭ አባላት ያሉት 45 የንቅናቄውን ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላትን በሚስጥር ድምፅ አሰጣጥም መርጦ ያፀደቀ ሲሆን የተመረጡት አባላትም የድርጅቱን ሊቀመንበርና ም/ሊቀመንበር መርጠዋል።
በዚህም መሰረት የአብን ሥራ አስፈፃሚ አመራሮች፦
• አቶ በለጠ ሞላ ሊቀመንበር
• አቶ የሱፍ ኢብራሂም ም/ሊቀመንበር
• አቶ አዲስ ኃረገወይን የፖሊሲ ስትራቴጂ ኃላፊ
• አቶ ጣሂር ሞሐመድ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ
• ዶ/ር ቴዎድሮስ ኃ/ማርያም የውጭ ጉዳይና ዓለማቀፍ ግንኙነት ኃላፊ
• አቶ ጋሻው መርሻ የአደረጃጀት ጉዳይ ኃላፊ
• አቶ መልካሙ ፀጋዬ የፅሕፈት ቤት ኃላፊ
• አቶ ጥበበ ሰይፈ የሕግና ስነምግባር ኃላፊ
• አቶ ክርስቲያን ታደለ የፓለቲካ ጉዳዮች ኃላፊ ናቸው፡፡
አቶ በለጠ ሞላ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህር ሲሆኑ የአብን ም/ሊቀ መንበርም ነበሩ፡፡