ልዩልዩ
አምስት ልጆቿን አንቃ የገደለችው ቤልጂየማዊት በፈቃደኝነት መገደሏ ተገለጸ
ቤልጂየም ሰዎች በፈቃደኝነት ስቅይ አልባ ሞት የመሞት መብትን ለዜጓቿ የሚፈቅድ ህግ አላት
ጀነቪቭ ለርሚት የተሰኘችው እንስት አምስት ልጆቿን በመግደል ራሷን ልታጠፋ ስትል በፖሊስ ተይዛ በእስር ላይ ነበረች
አምስት ልጆቿን አንቃ የገደለችው ቤልጂየማዊት በፈቃደኝነት መገደሏ ተገለጸ።
የ40 ዓመቷ ጀነቪቭ ለርሚት የሞሮኮ የዘር ግንድ ካለው ባለቤቷ ጋር በብራስልስ ስትኖር ነበር ።
ይሁንና ባለቤቷ ቤተሰቦቹን ለመጎብኘት ወደ ሞሮኮ በፈረንጆቹ 2007 ላይ በተጓዘበት ወቅት ከሶስት እስከ 14 ዓመት ያሉ አምስት ልጆቿን በማነቅ እና በስለት በመውጋት ህይወታቸው እንዲያልፍ ማድረጓን ቢቢሲ ዘግቧል።
- በአዲስ አበባ ሁለት ሕፃናትን በአሰቃቂ ሁኔታ የገደለችው ግለሰብ የሞት ቅጣት ተፈረደባት
- “አላዳንከኝም” በሚል ቀዶ ጥገና ያደረገለትን ዶክተር ጨምሮ ሶስት ሃኪሞችን የገደለው ታጣቂ
ይህች እንስት በመጨረሻም የራሷን ህይወት ለማጥፋት በቢላዋ አካሏን ብትወጋም ህመሙን መቋቋም ሲያቅታት ወደ ፖሊስ በመደወል እርዳታ መጠየቋ ተገልጿል።
በፈጸመችው ተደራራቢ ወንጀል ምክንያት የእድሜ ልክ እስር የተፈረደባት ይህች እንስት በፈቃደኝነት እንድትሞት መደረጓን በዘገባው ላይ ተጠቅሷል።
ቤልጂየም በረጅም ጊዜ ስቃይ ውስጥ የገቡ ሰዎች ስቃይ አልባ ሞት እንዲሞቱ የሚፈቅድ ህግ ያላት ሲሆን አምስት ልጆቿን በመግደሏ ጥልቅ ጸጸት ውስጥ የነበረችው ይህች እንስትም በራሷ ፈቀድ ከቀናት በፊት መገደሏ ተገልጿል።
በቤልጂየም በዚህ ህግ መሰረትም ቡተጠናቀቀው 2022 ዓመት ውስጥ ሶስት ሺህ ገደማ ሰዎች ከስቃያቸው ማገገም ባለመቻላቸው በፈቃደኝነት ህይወታቸው እንዲያልፍ ተደርጓል።