ራሷን በእሳት አቃጥላ የገደለችው ጋዜጠኛ ከመሞቷ በፊት ለሞቴ መንግስትን ተጠያቂ አድርጉ ብላ ነበር
ጋዜጠኛ ኢሪና ስላቪና በሩሲያ የሀገር ውስጥ ጉዳዮች ሚኒስቴር ፊት ለፊት ነበር ራሷን ያቃጠለችው
በአርታኢነት የምትሰራበት ኮዛ ፕሬስም ክስተቱን ያረጋገጠ ሲሆን ቀድሞ ህልፈቷን ይፋ ያደረገው ባለቤቷ መሆኑ ተገልጿል
በአርታኢነት የምትሰራበት ኮዛ ፕሬስም ክስተቱን ያረጋገጠ ሲሆን ቀድሞ ህልፈቷን ይፋ ያደረገው ባለቤቷ መሆኑ ተገልጿል
ሩሲያዊቷ ጋዜጠኛ ኢሪና ስላቪና ትናንትና በሩሲያ የሀገር ውስጥ ጉዳዮች ሚኒስቴር ኒዘህኒ ኖቨጎሮድ ቅርንጫፍ ፊት ለፊት ራሷን በእሳት አቃጥላ መሞቷን ባለቤቷ አስታውቋል፡፡
ጋዜጠኛ ኢሪና የኮዛ ፕሬስ አርታኢ የነበረች ሲሆን ራሷን ማጥፋቷ በዓለም አቀፍ ደረጃ እያነጋገረ ነው፡፡ በአርታኢነት የምትሰራበት ኮዛ ፕሬስም ይህንኑ ያረጋገጠ ሲሆን ቀድሞ ህልፈቷን ይፋ ያደረገው ባለቤቷ አሌክሴይ ሙራክታቭ ነው፡፡
የሩሲያ የደህንነትና የፖሊስ አባላት ከትናንት በስቲያ በምትኖርበት አፓርታማ ሄደው ብርበራ በማካሄድ ያገኙትን ይዘው መሄዳቸው ተዘግቧል፡፡ የሀገሪቱ የጸጥታ አባላት ፍላሽ፣የእርሷንና የልጇን ተንቀሳቃሽ ኮምፒዩተሮች (ላፕቶፖች) ፣የባለቤቷንና የእርሷ ስልኮችና ሌሎችም ከጋዜጠኛዋ ቤት መውሰዳቸው ገልጻ ነበር፡፡
ከዚህ ቀደም ብሎ የጸጥታ ሃይሎች ጋዜጠኛዋን ኦፕን ሩሲያ ድርጅት ለሚባል ድርጅት ሰነዶችን እንድትሰጥ ጠይቀዋት ነበር ተብሏል፡፡ የጸጥታ ሰዎች በጋዜጠኛዋ ቤት ብርበራ ያካሄዱትም ሚክሃይል ሎሲልቪች ከሚባለው የኒዘህኒ ኖቨጎሮዱ ባለሀብት እና የኦፕን ሩሲያ ድርጅት ባለቤት የወንጀክ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ነው ተብሏል፡፡
እርሷን የጸጥታ ሃይሎች ከሚሉት ድርጅት ጋር ምንም ግንኙነት እንደሌላት መግለጿ የሚታወስ ሲሆን ተቋሙ በሩሲያ ባላሥልጣናት እንደማይፈለግም በዘገባው ተጠቅሷል፡፡
ጋዜጠኛዋ በይፋዊ የፌስቡክ ገጿ ቀደም ብላ ለእኔ ሞት ተጠያቂው የሩሲያ መንግስት ነው ማለቷ አነጋጋሪ መሆኑን ትሌግራፍ ዘግቧል፡፡