ጆርድ ፍሎይድን የገደለው ፖሊስ የ22 ዓመት ከ6 ወር እስር ተፈረደበት
አቃቤ ህግ ግን የቀድሞው ፖሊስ በ30 ዓመት እስር እንዲቀጣ ፍርድ ቤቱን ጠይቆ ነበር
ደርክ ሾቪን የተባለው ፖሊስ የጆርድ ፍሎይድን አንገቱ ላይ በጉልበቱ በመቆም ህይወቱ እንዲያልፍ አድርጓል
በአሜሪካዋ ሚንሶታ ጆርድ ፍሎይድን የገደለው ፖሊስ ደርክ ሾቪን የ22 ዓመት ከ6 ወር እስር ተፈረደበት።
የቀድሞው የአሜሪካ ፖሊስ ደርክ ሾቪን በጥቁር አሜሪካዊው ጆርድ ፍሎይድ አንገት ላይ በመቆም ትንፋሽ አጥሮት እንዲሞት ማድረጉ ይታወሳል።
ይህ ፖሊስ ከአንድ ዓመት በፊት በፈረንጆቹ ግንቦት 25 ቀን 2020 ዓመት በአሜሪካዋ ሚኔሶታ ጆርድ ፍሎይድን ከመኪና ላይ በማውረድ እና አንገቱ ላይ በጉልበቱ በመቆም ህይወቱ እንዲያልፍ ያደረገው።
በዚህ ደርጊት ምክንያትም በዓለማችን የተለያዩ አገራት የተቃውሞ ሰልፎች ሲካሄዱ የቆ ሲሆን፤ የፍርድ ሂደቱም ጎን ለጎን ሲካሄድ ቆይቷል።
ድርጊቱን በመፈጸሙ ጥፋተኛ የተባለው ደርክ ሾቪን በትናንትናው ዕለት በሚኒሶታ ፍርድ ቤት ቀርቦ 22 ዓመት ከ6 ወር አስር እንደተፈረደበት ሲ.ጂ.ቲ.ኤን አፍሪካ ዘግቧል።
ፍርዱን ያስተላለፉት ዳኛ እንደተናገሩት “ፍርዱ በስሜት የተወሰነ አይደለም ይህ ፍርድ ለሟች ቤተሰቦች የህመም ስሜት እውቅና የሰጠ እና ህጉ የሚለው ነው የሆነው ” ብለዋል።
ክሱን የመሰረተው የሚኒሶታ የጠበቃ ቢሮ በበኩሉ ግድያውን በፈጸመው የቀድሞው ፖሊስ ደርክ ሾቪን የ30 ዓመት እስር እንዲፈረድበት ጠይቀው ነበር።
የ45 ዓመቱ የሚያናፖሊስ ፖሊስ ባልደረባ ደርክ ሾቪን በ46 ዓመቱ ጆርድ ፍሎይድ አንገት ላይ ለ9 ደቂቃ አንገቱ ላይ ከቆመበት በኋላ ነበር ሀይወቱ ያለፈው።
ይሄንን አሰቃቂ የጆርጅ ፍሎይድ ግድያ እያለቀሰች በእጅ ስልኳ በመቅረጽ ድርጊቱን ዓለም እንዲያውቀው ያደረገችው ዳርኔላ ፍሬዘር የምትባል የ17 ዓመት ታዳጊ ስትሆን ዓለም አቀፉ የሽልማት ተቋም የፑሊትዘር 2021 ዓመት የክብር ተሸላሚ አድርጓታል።