ቤልጂየም ሴተኛ አዳሪነትን ህጋዊ አደረገች
በዚህ ሙያ የሚሰማሩ ሰዎች ተገቢው የህግ ከለላ ተሰጥቷቸው ጡረታ እና ግብር ይከፍላሉ ተብሏል
አዲሱ ህግ ሴተኛ አዳሪዎች እንደ ማንኛውም ሙያ የስራ ስምምነት መፈጸም እንዲችሉ ይፈቅዳል
ቤልጂየም ሴተኛ አዳሪነትን ህጋዊ አደረገች፡፡
የአውሮፓ ህብረት መዲና የሆነችው ቤልጂየም የወሲብ ንግድን እንደ ማንኛውም ሌሎች ሙያዎች መስራት እንደሚቻል የሚፈቅድ ህግ አጽድቃለች፡፡
በዚህ ህግ መሰረት ወደ ወሲብ ንብግ ለመግባት ህጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ መያዝን እንደ መስፈርት ያስቀመጠች ሲሆን ህጉ በመጽደቁ አስቀድመው በድብቅ ሲሰሩ የነበሩ ተቋማት እና ግለሰቦች ደስተኞች መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
እንደ ዩሮ ኒውስ ዘገባ ከሆነ በወሲብ ንግድ የተሰማሩ ሰዎች አገልግሎቱን ለመስጠት ከተቋቋሙ ድርጅቶች እና ፈላጊዎች ጋር መዋዋል ይችላሉ ተብሏል፡፡
ለዓመታት በሴተኛ አዳሪነት የተሰማራች አንድ ስሟ ያልተጠቀሰ ሴት ለዩሮ ኒውስ እንዳለችው የወሲብ ንግድ በድብቅ ሲካሄድ ነበር ፍላጎት እስካለ ድረስ ስራውን በሀላፊነት እና በህጋዊነት መስራት የሚቻልበትን አሰራር መፍጠሩ ጥሩ መሆኑን ተናግራለች፡፡
በብራስልስ ከተማ የወሲብ ንግድ አገልግሎት የሚሰጥ ተቋም ያለው አሌክሳንድር ሞሪልስ በበኩሏ ስራውን በትክክል ወይም በተሳሳተ መንገድ እየሰራን መሆኑን አናውቅም ነበር ይህ ህግ መውጣቱ ጥሩ ነው ብላላች፡፡
የህጉ መውጣት በወሲብ ንግድ የተሰማሩ ሰዎች የጤና መድህን፣ የስራ ዋስትና እና ዓመታዊ እረፍት እንዲያገኙ የሚያስችል እንደሆነም በዘገባው ላይ ተጠቅሷል፡፡
እንዲሁም በወሲብ ንግድ በሚተዳደሩ ተቋማት ውስጥ ተቀጥረው የሚሰሩ ሰራተኞች ምቹ የስራ አካባቢ እና በአገልግሎት ፈላጊ ደንበኞች የሚደርስባቸውን አካላዊ እና ስነ ልቦናዊ ጉዳቶችን ከማስቀረት አንጻር ህጉ ጥቅም እንደሚሰጥም ተገልጿል፡፡
ወደ አውሮፓ የሚጓዙ ስደተኞች በተለይም ሴቶቹ ተገደው ወደ ወሲብ ንግድ እንዲገቡ ይደረግ ነበር የተባለ ሲሆን ይህ ህግ የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸውን ስደተኞች ቀጥሮ የተገኘ ተቋም ቅጣት ይጠብቀዋልም ተብሏል፡፡