የሂፕ ፖፕ ስልተ ምት ሙዚቃዎች የበለጠ ተመራጭ እንደሆኑ ተሳታፊዎች ተናግረዋል ተብሏል
ሙዚቃ እና ወሲብ ምን ያገናኛቸዋል?
ከመዝናኛዎ መካከል አንዱ የሆነው ሙዚቃ በወሲብ ወቅት የሚገኝ ደስታን እንደሚጨምር ጥናት አመልክቷል።
ዩሮ ኒውስ ዚፕ ሄልዝ የተሰኘ የጤና ተቋም ያወጣውን የጥናት ሪፖርት ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው ከሆነ ሙዚቃ እየሰሙ ወሲብ የሚፈጽሙ ሰዎች ሙዚቃ ከማይሰሙት በተሻለ መንገድ ደስተኛ እንደሚሆኑ ገልጿል።
እንደ ዘገባው ከሆነ በጥናቱ ከተሳተፉ 1 ሺህ ሰዎች መካከል 47 በመቶዎቹ በወሲብ ወቅት ሙዚቃ እንደሚሰሙ ተናግረዋል።
እንዲሁም 68 በመቶ ያህሉ ደግሞ በወሲብ ወቅት ሙዚቃ መስማታቸው ከፍርሀት ያድነናል ብለዋል።
ከጥናቱ ተሳታፊዎች መካከልም 63 በመቶ ያህሉ ሙዚቃ እየሰማን ወሲብ ስንፈጽም የቆይታ ጊዜያችን ይጨምርልናል ሲሉም ተናግረዋል ተብሏል።
በተለይም የፖፕ ስልተ ምት ያላቸው ሙዚቃዎች በወሲብ ወቅት የበለጠ ተመራጭ እንደሆኑ ተገልጿል።
በተለይም የዘር ሀረጉ ከኢትዮጵያ የሚመዘዘው ትውልደ ካናዳዊቱ ዘ ዊክኢንድ ሙዚቃዎች በብዙዎች በወሲብ ወቅት አብዝተው የሚመርጡት ሆኗል ተብሏል።
በነጠላ ሙዚቃ ደግሞ የአሜቲካዊቷ ድምጻዊ ኒኪ ሚናጅ "ሱፐር ፍሪኪ ገርል" የተሰኘው ሙዚቃ በጥናቱ ከተሳተፉ ሰዎች መካከል አብዛኞቹ በወሲብ ወቅት የሚመርጡት ሙዚቃ እንደሆነ ተናግረዋል።
ከሁሉም ግን ክላሲካል ሙዚቃዎችን የሚሰሙ ወሲብ የሚፈጽሙ ሰዎች የበለጠ ደስታን የሚያገኙ እንደሆኑ በዘገባው ላይ ተጠቅሷል።