የወሲብ ማነቃቂያ መድሀኒት (ቪያግራ) ያለ ሀኪም ትዕዛዝ የወሰደው ግለሰብ ለአይነ ስውርነት ተዳረገ
የ32 ዓመቱ ኢራናዊ የወሲብ ማነቃቂያ መድሀኒትን ከመጠን በላይ ወስዷል ተብሏል
የህክምና ባለሙያዎች መድሀኒቱን ያለ ባለሙያ ትዕዛዝ መውሰድ ለብዙ ችግሮች ይዳርጋል ብለዋል
የወሲብ ማነቃቂያ መድሀኒት (ቪያግራ) ያለ ሀኪም ትዕዛዝ የወሰደው ግለሰብ ለአይነ ስውርነት ተዳረገ።
የ32 ዓመቱ ኢራናዊ የወሲብ ማነቃቂያ ወይም ቪያግራ የተሰኘውን መድሀኒት አብዝቶ በመውሰዱ ምክንያት እይታውን አጥቷል ተብሏል።
እንደ ዴይሊሜይል ዘገባ ስሙ ያልተጠቀሰው ኢራናዊ ከህክምና ትዕዛዝ ውጪ ከመጠን በላይ በመውሰዱ ምክንያት ማየት እንዳልቻለ ተገልጿል።
ግለሰቡ 100 ግራም መጠን ያለው ቪያግራ መድሀኒት በወሰደ ከ3 ሰዓት በኋላ የቀኝ አይኑ ማየት ማቆሙን ተናግሯል።
አንድ አይኑ ማየት ማቆሙን ተከትሎ ወደ ህክምና ተቋም የሄደው ይህ ግለሰብ ለእይታ የሚያግዙ የደም ስሮቹ አብጠው መፈንዳታቸው በተደረገለት የስካን ህክምና ተረጋግጧል ተብሏል።
ግለሰቡ ከአይኑ በተጨማሪም በሰውነቱ ያሉ የተለያዩ የደም ስሮች ያለቅጥ ተለጥጠው እንደተጎዱም ተገልጻል።
የዚህ ኢራናዊ እይታ ማጣትን ተከትሎ የህክምና ባለሙያዎች ሰዎች ያለ ሐኪም ትዕዛዝ የትኛውንም መድሀኒት መውሰድ እንዳይወስዱ ሲሉ አሳስበዋል።