ሩሲያ የቅርብ አጋሯ የሆነችውን ቤላሩስ “የሚሳኤል ባለቤት እንድትሆን” እርዳታ ልታደርግ ነው ተባለ
የቤላሩስ ፕሬዝዳንት ሉካሼንኮ "ከሩሲያው ኢስካንደር ሞዴል ጋር የሚመሳሰል አዲስ ሚሳኤል እየፈጠርን ነው" ብሏል
ሩሲያ "ልዩ ኦፕሬሽን" በሚል በዩክሬን እያካሄደችው ባለው ወታደራዊ ዘመቻ ኢስካንደር ሚሳኤሎችን ተጠቅማለች
ሩሲያ የቅርብ አጋሯ የሆነችውን ቤላሩስ “የሚሳኤል ባለቤት እንድትሆን” እርዳታ ልታደርግ ነው ተባለ፡፡
የቤላሩስ ፕሬዝዳንት አሌክሳንደር ሉካሼንኮ ከሀገሪቱ የመከላከያ መኮንኖች ሰብስበው እንደተናገሩት፤ ቤላሩስ ከሩሲያው ኢስካንደር ጋር የሚመሳሰል ሚሳኤል እንድታመርትና የጦር ኃይሏን እንድታጎለብት ሞስኮ ተስማምታለች ብሏል፡፡
ሉካሼንኮ ፤ የዩክሬኑ ጦርነት ሁኔታ ዘመናዊ፣ በጣም ውጤታማ መሳሪያ እና ወታደራዊ ሎጂስቲክስ ይዞ መቆየት አስፈላጊ መሆኑ የሚያመላክት ነው ማለታቸውም የቤላሩሱ በልታ የዜና አገልግሎት ዘግቧል፡፡
በዚህም ሚንስክ የራሷ የሆነ ሚሳኤል ለማምረት የሚያስችላት አቅም ለመገንባት ከሩሲያ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደምታገኝ ሩሲያው ፕሬዝዳንት ቪላድሚር ፑቲን አረጋግጠውልኛል ሲሉ ሉካሼንኮ ተናግሯል፡፡
"ከኢስካንደር ሞዴል ጋር የሚመሳሰል በጣም ውጤታማና አዲስ ሚሳኤል እየፈጠርን ነው" ሲሉም ለቤልታ ተናግሯል ሉካሼንኮ።
ሉካሼንኮ፤ ፑቲን ለሩሲያ የጠፈር ኤጀንሲ ሮስስኮስሞስ ኃላፊ ዲሚትሪ ሮጎዚን ለቤላሩስ ተገቢውን ድጋፍ እንዲሰጡ ነግረዋቸዋልም ብሏል፡፡
ሩሲያ "ልዩ ኦፕሬሽን" በሚል በዩክሬን እያካሄደችው ባለው ወታደራዊ ዘመቻ ኢስካንደር ሚሳኤሎችን ተጠቅማለች።
ቤላሩስ የሩስያ የቅርብ አጋር ናት ብትሆንም ፤ ሉካሼንኮ በመጋቢት ወር የቤላሩስ የጦር ሞስኮ እያካሄደችው ላለ ኦፕሬሽን የሚሰተው ድጋፍ እንደሌለ መናገራቸው ይታወሳል፡፡
ፕሬዝዳንት ሉካሼንኮ ከዩክሬን ጋር ድንበር የምትጋራው እንዲሁም የሞስኮ ጠንካራ አጋር የሆነችው ቤላሩስ፤ በሁለቱ ወገኖች መካከል የሰላም ስምምነት እንዲፈጠር ግፊት እያደረገች መሆኑን ከቀናት በፊት መግለጻቸው የሚታወስ ነው።
የሩሲያ-ዩክሬን ጦርነት እንዲበቃ ቤላሩስ የተቻላትን ሁሉ በማድረግ ላይ ናትም ብሏል ፕሬዝዳንቱ፡፡
በሁለቱም ሀገራት መካከል የተጀመረው ድርድር ሚበረታታ ነው ያሉት ሉካሼንኮ "ምንም አይነት ጦርነት በፍጹም አንቀበልም ”ሲሉም አክሏል ።