“የዓለም ፍጻሜ ይሆናል” በሚባለው የኒኩሌር ጦርነት ወቅት አውሮፕላኑ የፕሬዝዳንት ፑቲን ማዘዣ ሆኖ ያገለግላል
የኒኩሌር የጦር መሳሪያን መቋቋም የሚችለው እና “የምጽአት ቀን” (ዶምስዴይ) የሚል መጠሪያ የተሰጠው የሩሲያ አውሮፕላን።
በሩሲያ “ኢሊዩሺን አይ.ኤል-80” የሚል መጠሪያ ያለው አውሮፕላኑ የዓለም ፍጻሜ ሊሆን ይችላል ተብሎ በሚነገርለት የኒኩሌር ጦርነት ወቅት የሩሲያ ፐሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ያለምንም ችግር ሀገሪቱን እንዲመሩ ያስችላቸዋል ተብሏል።
እንዲሁም ፕሬዝዳንቱ ጦራቸው የኒኩሌር ማሳሪያ ጥቃት እንዲፈጽሙ ትእዛዝ እንዲሰጡ የሚያስችላለቸው መሆኑንም ነው የተገለፀው።
ትንሹ የሩሲያ ቤተ-መንግስት (ክሬምሊን) ነው የተባለለት አውሮፕላኑ በኒኩሌር ጥቃት ወቅት ፕሬዝዳንት ፑቲን ከየትኛውም የኒኩሌር ጉዳት ለመጠበቅ የሚረዳ ነው ተብሏል።
“የምጽአት ቀን” አውሮፕላን የሚባለው ኢሊዩሺን አይ.ኤል-80 የመጀመሪያ በረራውን በፈረንጆቹ በ1987 ያደረገ ሲሆን፤ በ2008 ደግሞ የማሻሻያ እና ማዘመኛ ስራዎች ተሰርተውለታል።
የአውሮፕላኑ ቁመት 60 ሜትር የሚረዝም ሲሆን፤ የክንፉ ስፋት ደግሞ 48 ሜትር ነው።
በአየር ላይ እያለ ነዳጅ ሚሞላለት አውሮፐልኑ በሰዓት 850 ኪሎ ሜትር ፍጥነት እንደሚጓዝ እና ያለማቋረጥ ከ3 ሺህ 600 ኪሎ ሜትር በላይ የሚበር መሆኑ ተነግሯል።
በኢሊዩሺን ኩባያ የተመረተው አውሮፕላኑ ኩዝኔቶቭ ኤን ኬ-86 የተባለ ሞተር የሚጠቀም ሲሆን፤ አሁን ላይ ሩሲያ በአጠቃላይ 4 ምጽአት ቀን አውሮፕላኖች አሏት።
የአሜሪካ “የምጽአት ቀን” አውሮፕላን
አሜሪካም ከሩሲያ “የምጽአት ቀን” (ዶምስዴይ) አውሮፕላን ጋር የሚገዳደር የኒኩሌር ጦርነትን የሚቋቋም አውሮፕላን እንዳላት ከዚህ ቀደም መዘገባችን ይታወሳል።
“GRIM99” የሚል መለያ ኮድ ያለው አውሮፕላኑ “በራሪው ፔንታጎን” የሚል ቅጽል ስም ያለው ሲሆን፤ በኒኩሌር ጦርነት ወቅት የዘመቻዎች መዘዣ ማዕከል በመሆን ያገለግላል ተብሏል።
የቦይንግ 747 ምርት አውሮፕላኑ ብሄራዊ የአደጋ ጊዜ የአየር ማዘዣ ማእከል በሚል ይፋዊ ስሙ የሚታወቅ ሲሆን፤ አራት መሰል አውሮፕላኖች ብቻ ናቸው ያሉት።
አውሮፕላኑ በአየር ወለዶች በሰማይ ላይ እያለ ነዳጅ እየተሞላለት ያለማቋረጥ ለ150 ሰዓታት መብረር ይችላል የተባለ ሲሆን፤ አራት የጄነራል ኤሌክትሪክ ሞተሮች እና በጣም ከፍተኛ መጠን የመያዝ አቅም ያለው የነዳጅ ታንከርም ተገጥሞለታል።
67 ሳተላይት ዲሾች የተገጠሙለት አውሮፕላኑ፤ ይህም የመከላከያ ሚኒስትሩ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ከሚገኙ የአሜሪካ የጦር መርከቦች፣ ሰርጓጅ መርከቦች፣ የአየር እና የመድር ጦር ኃይሎች ጋር ለመገናኘት የሚያስችላቸው ነው።