በፈረንጆቹ 1972 አገልግሎት መስጠት የጀመረው ሄሊኮፕተሩ አሁን ላይ በ30 ሀገራት ጥቅም ላይ እየዋለ ነው
ሩሲያ ሰራሽ የሆነው ኤም.አይ-24 የጥቃት መሰንዘሪያ ሄሊኮፕተር እያጠቃ መብረር በመቻሉ “በራሪው ታንክ” የሚል መጠሪያ ተሰጥቶታል።
ኤም.አይ-24 ተለዋዋጭ ዲዛይን ኖሮት የተሰራ ሲሆን፤ ይህም በጦርነት ወቅት በጠላት ላይ ጥቃትን መሰንዘርን ጨምሮ ለትራንስፖርት አገልግሎት እንዲውልም ያስችለዋል።
ሄሊኮፕተሩ ወደ መሬት በጣም በመቅረብ ጥቃት እየሰነዘረ መብረር ይችላል የተባለ ሲሆን፤ ይህም “በራሪው ታንክ” የሚለውን መጠሪያ እንዳሰጠው ይነገራል።
“በራሪው ታንክ” ሄሊኮፕተሩ ካለው ሁለገብ የተለዋዋጭነት ባህሪ አንጻር በሚያስደንቅ የጦር መሣሪያ የታጠቀ መሆኑን ቢዝነስ እንሳይደር በድረ ገጹ ያወጣው መረጃ ያመለክታል።
ሄሊኮፕተሩ ከሚታጠቃቸው መሳሪያዎች መካከልም
ፀረ-ታንክ ሚሳዔሎች
የሮኬት ማስወንጨፊያ
አውቶማቲክ ጠብመንጃዎች
የቦምብ መጣያዎች እና ሌሎችም ዘመናዊ መሳሪያዎችን መታጠቅ ይችላል ተብሏል።
“በራሪው ታንክ” ሄሊኮፕተር እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር በ1972 በወቅቱ የሶቪየት ህብረት የአየር ኃይል ለመጀመሪያ ጊዜ በጥቅም ላይ መዋል እንደጀመረ መረጃዎች ይጠቁማሉ።
ሄሊኮፕተሩ በአሁኑ ወቅት ከ30 በላይ ሀገራት ውስጥ ጥቅም ላይ እየዋለ ሲሆን፤ ሁለገብ አገልግሎት የሚሰጥ መሆኑ በብዙዎች ተመራጭ እንዳደረገው ይነገራል።
ሩሲያ ኤም.አይ-24 በተጨማሪም ኤም.አይ-25 እና ኤም.አይ-35 የሄሊኮፕተሩን ስሪቶች በብዛት በማምረት ለውጭ ገበያ እንደምታቀርብም ይታወቃል።