የሩሲያ "ሰላይ" ነው ተብሎ የሚጠረጠረው አሳ ነባሪ ሞቶ ተገኘ
ህቫልድሚር በሚል ስያሜ የሚጠራው ይህ አሳ ነባሪ በሩሲያ እና ኖርዌይ ድንበር ላይ ሞቶ ተገኝቷል
ኖርዌይ የሞተውን አሳ ነባሪ አካል በሙውሰድ ምርምር እንደምታደርግበት አስታውቃለች
የሩሲያ "ሰላይ" ነው ተብሎ የሚጠረጠረው አሳ ነባሪ ሞቶ ተገኘ።
ምዕራባዊያን ሀገራት ሩሲያ አሳ ነባሪን በማሰልጠን የአርክቲክ ሀገራትን እየሰለለች ነው ሲሉ ይደመጣል።
ሀገራቱ ይህንን እንዲሉ ያስቻላቸው ደግሞ ነጩ አሳነባሪ ሩሲያ ከኖርዌይ እና ስዊድን ጋር በምትዋሰንባቸው አካባቢዎች በመታየቱ ነበር።
ይህ አሳ ነባሪ ወገቡ ላይ ሰው ሰራሽ ቁስ መታየቱ፣ አሳ ነባሪው በተለየ መንገድ ለሰዎች ፍቅር ያለው መሆኑ የሩሲያ ሰላይ ነው እንዲባል ምክንያት ሆኗል።
ሩሲያ በበኩሏ አሳ ነባሪው ለስለላ ስራ ስልጠና በመስጠት አሰማርተዋለች መባሏን አስተባብላለች።
በአርክቲክ ውሀማ አካባቢዎች በተደጋጋሚ የሚታየው ይህ አሳ ነባሪ ምን አልባት ከእንስሳት መንከባከቢያ ስፍራ ያመለጠ ሊሆን እንደሚችል ግምቷን ተናግራለች።
ይሁንና ይህ ብዙ የተባለለት ነጩ አሳነባሪ በሩሲያ እና ኖርዌይ ባህር ላይ አሳ እያጠመዱ የነበሩ አባት እና ልጅ አግኝተውታል ሲል ዘ ጋርዲያን ዘግቧል።
ይህ አሳ ነባሪ ለሩሲያ ይሰልላል መባሉን ተከትሎ ህቫል የሚለውን የኖርዌይ ቋንቋ እንዲሁም የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ስምን. በመውሰድ "ህቫልዲሚር" የሚል ስያሜ ተሰጥቶት ነበር።
የእንስሳት አፍቃሪ ሰዎች በዚህ አሳ ነባሪ ሞት ምክንያት ማዘናቸውን ገልጸው እንስሳቱ እስከ ባለፈው አርብ ድረስ ጤናማ እንደነበር ተናግረዋል።
ሩሲያ በበኩሏ ስለ አሳነባሪው አሟሟት የምታውቀው ነገር እንደሌለ ገልጻ እንስሳትን ለውትድርና ተግባራት መጠቀም እንደማይገባ አስታውቃለች።