አሳ ነባሪው የባህሩ የላይኛው አካል ላይ ከወጣ በኋላ ሚሼልን ተፎቶታል
ሚሼል ፓካርድ ይባላል፤ በአሜሪካዋ ማሳቹሴትስ ነዋሪ ሲሆን በአሳ አጥማጅንት ነው ኑሮውን የሚገፋው።
አሳ አጥማጁ ግለሰብ “ሎብስተር” የተሰኘ አሳ የማጥመድ ልማድ ያለው ሲሆን፣ አሳውን በማሰስ ላይ እያለ ያልጠበቀው ነገር ይከሰታል።
የ56 ዓመቱ ሚሼል ፓካርድ “ሎብስተር” የተሰኘ የአሳ ዝርያ ለማጥመድ ከባህር ስር 13 ሜትር ገደማ ጠለቆ እያለ የአሳ ነባሪ እንደዋጠው ይናገረል።
በአሳ ነባሪው ሆድ ውስጥም ከ30 እስከ 40 ሰከንድ መቆየቱን የሚናገረው ሚሼል፣ በአሳ ነባሪው ሆድ ውስጥ በቆየበት ጊዜ ሁሉም ነገር ጨለማ ሆኖ ይታየው እንደነበረ ተናግሯል።
ሆኖም ግን ሚሼል ባህር ስር ሲጠልቅ ከሚጠቀምበት መተንፈሻ መሳሪያ በመያዙ በአሳ ነባሪው ሆድ ውስጥ እያለም ይተነፍስ እንደነበረ ገልጿል።
በመጨረሻም አሳ ነባሪው የባህሩ የላይኛው አካል ላይ ከወጣ በኋላ ሚሼልን የተፋው ሲሆን፣ አሳ ነባሪው ከተፋው በኋላም አብረውት ይሰሩ የነበሩ ጓደኞቹ እንደታደጉት ነው ያብራራው።
“ሰውነቴ ላይ ከፍተኛ መጫጫር ደርሶብኛል” ያለው ሚሼል፣ በአጥንቱ ላይ ግን ምንም አይነት የመሰበር አደጋ እንዳልገጠመው አስታውቋል።
የማሳቹሴትስ የአሳ ነባሪ ጥናት ተቋም ዳይሬክተር ጆክ ሮቢንስ፣ ከዚህ ደቀም እንዲህ አይነት ነገር ሰምታ እንደማታውቅ የተናገረች ሲሆን፤ ነገር ግን ግለሰቡ ያለቦታው በመገኘቱ አደጋው እንደተከሰተ ትናገራልች።