በሽር አል-አሳድ በፈረንጆቹ ሃምሌ 17/2000 አባታቸውን ኃፌዝ አል አሳድን በመተካት በትረ ስልጣን እንደጨበጡ እስካሁን ይመራሉ
የሶሪያው ፕሬዚዳንት በሽር አል አሳድ ለ4ኛ ጊዜ ለቀጣይ ሰባት ዓመታት ሀገሪቱን በፕሬዝዳንትንት ለመምራት ዛሬ ቃለ-መሃላ ፈጽመዋል፡፡የቃለ-መሃላ ሥነ-ሥርዓቱ ደማስቆ ከተማ ከሚገኘው ቤተ መንግስት በቀጥታ በሀገሪቷ የቴሌቪዥን ጣቢያ ተላልፈዋል፡፡
በቃለ መሃላ ስነስርዓቱ ላይ የሀገሪቱ የሃይማኖት አባቶች ፣ የፓርላማ አባላት ፣ የፖለቲካ ሰዎች እና የጦር መኮንኖች መገኘታቸውም ሲጂቲኤን የዘገበው።
የ55 ዓመቱ በሽር አል-አሳድ በቅርቡ በተካሄደው ምርጫ 95.1 የህዝብ ድምፅ በማግኘት ማሸነፋቸው ይታወሳል፡፡
ፕሬዝዳንቱ በሀገሪቱ ያለውን የደከመ ኢኮኖሚ እንዲያንሰራራ በቀጣይ የስልጣን ዘመናቸው ለኢንቨስትምንትና ምርታማነት እድገት እንዲሁም ሙስናን ለመከላከል ትኩረት ሰጥተው እንደሚሰሩ ተናግሯል፡፡
አሳድ ማእቀቦች ቢኖሩም ሃገሪቱ በታዳሽ ኃይሉ መስክ ትርፋማ ለመሆን የምታደርገው ጥረት አይገታውም ሲሉም ነው የተደመጡት፡፡
በታዳሽ ኃይል ላይ መዋእለ ንዋያችን የምናፈሰው የኃይል አቅርቦት ፍላጎትን ከማማዋላጽ በዘለለ ለኢንቨስትመንት የጎላ ፋይዳ አለውም ነው ያሉት በሽር አል አሳድ፡፡አሳድ ሙስናን ለመከላከል አዲስ የመታገያ እና ሙሰኞችን ለማጋለጥ የሚያስችል መንገድ እንደሚዘይዱም የሲጂቲኤን ዘገባ ያመለክታል፡፡
የተባበሩት መንግስታት መረጃ እንደሚመለከተው ከሆነ 80 በመቶ የሚሆኑት ሶርያውያን ከድህንት ወለል በታች ይኖራሉ፡፡
በሽር አል አሳድ እንደፈረንጆቹ ሃምሌ 17/2000 አባታቸውን ኃፌዝ አል አሳድን በመተካት የሶርያ በትረ ስልጣን እንደጨበጡ አስካሁን እየመሩ ያሉ ፕሬዝዳንት ናቸው፡፡
እንደፈረንጆቹ 2012 የፀደቀው የሶርያ ህገ-መንግስት አንድ ፕሬዝዳንት መምራት የሚችላው ሁለት ጊዜ ሲሆን የአሁኑ የአል አሳድ ቆይታ የመጨረሻ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ሶርያ በከባድ ቀውስ ውስጥ ከተዘፈቀች 10 ዓመታት አስቆጥራለች፡፡ የውጭ ኃይሎች ጣልቃ ገብነት፣ ማእቀብና የሽብር መጫን ሀገሪቱ እዚህ ደረጃ እንድትደርስ አሉተዊ አስተዋጽኦ እንደነበራቸው የፖለቲካል ሳይንስ ልሂቃን ሲያነሱ ይሰተዋላል፡፡