የዩኤኢ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ላለፉት 10 ዓመታት በእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ ያለቸው ሶሪያ ወደ ቀደመ ሰላሟ ትመላሳለች ብለዋል
የዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ(ዩኤኢ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሼህ አብዱላህ ቢን ዛይድ አል ናህያን
ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ከሩሲያ አቻቸው ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል።
ሚኒስትሩ በዚህ ጊዜ እንዳሉት ላለፉት 10 ዓመታት በእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ ያለቸው ሶሪያ ወደ ቀደመ ሰላሟ መመለሷ የማይቀር ነው ብለዋል።
ሼህ አብዱላህ ቢን ዛይድ ከላቭሮቭ ጋር በነበራቸው ተጨማሪ ውይይትም ሩሲያ የሀገራቸው ቁልፍ አጋር እንደሆነች እና የሁለቱ አገራት ግንኙነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መሆኑንም ተናግረዋል።የተባበሩት አረብ ኢምሬት ከሩሲያ ጋር ባላት የኢኮኖሚ ትስስር መርካታቸውን የተናገሩት ሚኒስትሩ የኮሮና ቫይረስ ከመከላከል አንጻርም በትብብር እየሰሩ መሆኑን ተናግረዋል።
ሼህ አብዱላህ ቢን ዛይድ አክለውም ሀገራቸው ከዓለም አገራት ጋር ጥሩ ግንኙነት መመስረት ትፈልጋለች ያሉ ሲሆን ከሩሲያ ጋር ያላቸውን ወዳጅነት መተማመን ላይ የተመሰረተ እንደሆነ ገልጸዋል።
የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ሰርጊ ላቭሮቭ በበኩላቸው ከተባበሩት አረብ ኢመሬቶች ጋር በሁለቱ አገራት ቀጣይ ወዳጅነት ዙሪያ መምከራቸውን ገልጸዋል።
ሩሲያ ከተባበሩት አረብ ኢምሬቶች ጋር በሩሲያ ኢንቨስትመንት ፈንድ በኩል እና በኮሮና ቫይረስ ክትባት ማምረት ዙሪያ በትብብር መስራታቷን እንደምትቀጥልም ተናግረዋል።
ላቭሮክ አክለውም በሶሪያ፤ሊቢያ እና የመን የፖለቲካ መረጋጋት እንዲመጣ ሀገራቸው ድጋፍ ታደርጋለች ያሉ ሲሆን የተባበሩት አረብ ኢምሬት ከእስራኤል ጋር የጀመረችውን የሰላም ስምምነት እንደሚደግፉትም አክልዋል።