የሆቴል ባለሙያዎች እና ተጓዦች ደረጃ ከሚመድቡ አካላት መካከል ዋነኞቹ ናቸው
የዓለማችን ምርጥ 10 ሆቴሎች እነማን ናቸው?
የሆቴል ኢንዱስትሪ ሰፊ የሰው ሀይል በመቅጠር እና በሌሎች የኢኮኖሚ አበርክቶዎቹ ይታወቃል።
በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ተጎድቶ የቆየው የሆቴል ኢንዱስትሪ አሁን ላይ ወደ ቀድሞ ሁኔታው ስለመመለሱም ተገልጿል።
በዓለም ላይ ያሉ የሆቴሎችን ደረጃ በማውጣት እና በቱሪዝም አማካሪነቱ እሚታወቀው ሌግዠሪ ሆቴሎች ኩባንያ በያዝነው 2023 ዓመት ምርጥ ሆቴሎችን ደረጃ ይፋ አድርጓል።
በዓለማችን ያሉ ሁሉም ሆቴሎች በውድድሩ ተሳትፈዋል የተባለ ሲሆን ምርጥ 50 የዓለማችን ሆቴሎችን ይፋ አድርጓል።
የሆቴል ደረጃውን በየሀገሩ በመጓዝ የሚታወቁ ጎብኚዎች፣ የሆቴል ባለሙያዎች እና የቢዝነስ ሰዎች በሰጧቸው ነጥቦች መሰረት ተደርጎ ወጥቷል ተብሏል።
እንደ ሲኤን ኤን ዘገባ መመዘኛ መስፈርቶቹ ሆቴሎቹ የተገነቡበት ቦታ ከተፈጥሮ ጋር ያለው ትስስር፣ የግንባታ ዲዛይን፣ አገልግሎት አሰጣጥ እና ሌሎችም ዋና ዋና መስፈርቶች ናቸው።
በዚህ መሰረትም የጣልያኑ ፓሳላኳ ሆቴል የዓለማችን ምርጡ ሆቴል ሲባል የሆንግኮንጉ ሮዝውድ እንዲሁም የታይላንዱ ፎርሲዝንስ ሆቴል ሶስተኛ ደረጃን ይዟል።
አፍሪካዊቷ ሞሮኮ ላማሞሚያ የተሰኘው ሆቴል የዓለማችን ስድስተኛው ምርጡ ሆቴል ተብሎ ተመርጧል።