የ25 ዓመት እስር ተፈርዶባቸው የነበሩት የ"ሆቴል ሩዋንዳ" ጀግና ከእስር ተለቀቁ
ፖል ሩሴሳባጊና የሆቴል ስራ በነበረበት ወቅት 1 ሺህ 200 ዜጎችን በወቅቱ ከነበረው የእርስ በርስ ግድያ ታድገዋል ተብሏል
ፕሬዝዳንት ፖል ካጋሚ ግለሰቡን ከእስር እንዲለቀቁ ወስነዋል ተብሏል
የ25 ዓመት እስር የተፈረደባቸው የ"ሆቴል ሩዋንዳ" ፊልም ሀሳብ መነሻ ጀግና ከእስር ተለቀቁ።
ለታዋቂው የሆሊውድ ፊልም "ሆቴል ሩዋንዳ" ታሪክ መነሻ የሆኑት ፖል ሩሴሳብስጊና በሩዋንዳ አማጺያንን በመርዳት ወንጀል ተጠርጥረው ነበር በኪጋሊ በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋሉት።
የሀገሪቱ ፍርድ ቤትም የ25 ዓመት እስር የፈረደባቸው ሲሆን ከሁለት ዓመት የእስር ጊዜ በኋላ ተለቀዋል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።
የ68 ዓመቱ ፖል በፈረንጆቹ 1994 ላይ በኪጋሊ ባለ አንድ ሆቴል ውስጥ በስራ አስኪያጅነት ይሰሩ በነበረበት ወቅት 1 ሺህ 200 ዜጎችን በወቅቱ ከነበረው የእርስ በርስ ግድያ ታድገዋል ተብሏል።
አሜሪካ ይህን የቀድሞ የሆቴል ስራ አስኪያጅ ከእስር እንዲለቀቅ በተደጋጋሚ ስትወተውት የቆየች ሲሆን በመጨረሻም የፖል ካጋሜ መንግሥት ተዋናዩን ከእስር ለቋል።
ለ100 ቀናት በዘለቀው የሩዋንዳ እርስ በርስ ጦርነት ከ800 ሺህ በላይ ዜጎች መገደላቸው ይታወሳል።
ይህ ግለሰብ የእርስ በርስ ጦርነቱ በቆመ በዓመቱ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆርጅ ቡሽ መንግሥት የነጻነት ሜዳሊያ ሽልማት ተበርክቶለታል።
የፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜ ዋነኛ ተቺ እንደሆነ የሚነገርለት ይህ ግለሰብ ንጹሀንን ከመገደል በማትረፉ ለምን ሊታሰር እንደቻለ እስካሁን ግልጽ አይደለም ተብሏል።
የግለሰቡ ታሪክ የማረካቸው የፊልም ሰሪዎች በፈረንጆቹ 2004 ላይ ታሪኩን ወደ ፊልምነት ቀይረውት ተወዳጅነት ማትረፍ ችሏል።
ይሁንና የሩዋንዳ መንግሥት ግን ግለሰቡ ለእስር የተዳረገው በዘር ማትፋት ወንጀል ሳይሆን በ2018 እና 2019 አማጺ ቡድኖችን ረድተዋል በሚል ወንጀል ተጠርጥረው እንደሆነ አስታውቋል።