ምድር ውስጥ ብቻ የተገነባው የዓለማችን ጥልቁ ሆቴል
ሆቴሉ ከመሬት ወደ ውስጥ የ419 ሜትር ርቀት አለው ተብሏል
በዚህ ጥልቅ ሆቴል ለአንድ አዳር አልጋ ለመያዝ 688 ዶላር መክፈል ይጠበቅቦታል
ምድር ውስጥ ብቻ የተገነባው የዓለማችን ጥልቁ ሆቴል
የስዊድኑ ሳላ ሲልቨር የተሰኘው ሆቴል ከመሬት ወደ ውስጥ 154 ሜትር ርቀት ላይ ተገንብቶ ዓለምን ጉድ አስብሎ ነበር፡፡
አሁን ደግሞ በዌልስ ወደ ውስጥ 419 ሜትር ርቀት ላይ የተገነባ ሆቴል ከአንድ ወር በፊት ተመርቋል፡፡
ሆቴሉ በተለይም ቅዳሜ ምሽት ላይ የአዳር መኝታ አገልግሎት መስጠት የጀመረ ሲሆን ለአንድ አዳርም 688 ዶላር እንደሚያስከፍል አስታውቋል፡፡
ሆቴሉ በብዛት የውጪ ወይም ቴክአዌይ አገለግሎት የሚሰጥ ሲሆን ቅዳሜን በተለየ መንገድ መዝናናት ለሚፈልጉ ደንበኞች ግን ልዩ አገልግሎት እንደሚሰጥ ገልጿል፡፡
ምንም ነገር በማይሰማበት ጥልቅ ጉድጓድ ውስጥ የተገነባው ይህ ሆቴል አራት ጥንድ አልጋዎች ያሉት ሲሆን ከመሬት ወደ ሆቴሉ ለመግባት በመሬት ውስጥ ለተወሰኑ ደቂቃዎች በእግር መጓዝ የግድ ነው ተብሏል፡፡
ሆቴሉ ምድር ውስጥ መገንባቱን ተከትሎ ቅዝቃዜው ለደንበኞች አመቺ ሆኖ መገንባቱ የተገለጸ ሲሆን ትንሽ ለብ ያለ ነገር ብቻ መጠጣት እንደሚፈቀድ ተገልጿል፡፡
የ4ጂ ኢንተርኔት፣ ሙቅ ነገሮች እና ሌሎች የሆቴል አገልግሎቶችን ለደንበኞቹ መስጠት የጀመረው ይህ ሆቴል በአጭር ጊዜ ውስጥ ደንበኞቹ ደርተውለታል ተብሏል፡፡