በ1 ሚሊየን የምርጫ ጣቢያዎች ድምጻቸውን የሚሰጡ ህንዳውያን 543 የምክርቤት አባላትን ይመርጣሉ
በአለማችን በህዝብ ብዛታቸው በቀዳሚነት ከተቀመጡት 10 ሀገራት ሰባቱ በዚህ አመት ምርጫ ያደርጋሉ።
አሜሪካ፣ ኢራን፣ ሩሲያ እና ህንድ የሚያደርጓቸው ምርጫዎችም የአለምን ፖለቲካዊ እና ምጣኔ ሃብታዊ እንቅስቃሴ ይወስናሉ ተብሎ ይጠበቃል።
የህዝብ ብዛት መሪነትን ከቻይና የተረከበችው ህንድ ከሚያዚያ 19 ሽከ ሰኔ 1 2024 ለስድስት ሳምንታት የሚዘልቅ የአለማችን ግዙፉን ምርጫ ለማካሄድ ቀጠሮ ይዛለች።
የህንድ ምርጫ ኮሚሽን እንዳስታወቀው በጠቅላላ ምርጫው 969 ሚሊየን ሰዎች ድምጽ ለመስጠት ተመዝግበዋል፤ አሃዙ ከአውሮፓ ህዝብ የሚልቅ፤ ከአለም ህዝብም ከ10 በመቶ በላይ ነው።
ረጅም ጊዜ በሚወስደውና ፓርቲዎችም ለምርጫ ቅስቀሳና ለሌሎች ጉዳዮች ከፍተኛ ወጪ በሚያወጡበት ምርጫ የጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ባሃራቲያ ጃናፓ ፓርቲ (ቢጄፒ) እንደሚያሸንፍ ተገምቷል።
ስለአለማችን ውዱና ረጅሙ ምርጫ ቀጥሎ በቀረበው ስእላዊ መረጃ በዝርዝር ይመልከቱ፦