ዶናልድ ትራምፕ ስምንት እጩ ምክትል ፕሬዝዳንቶችን አጩ
ከሳምንታት በፊት በ34 ክሶች ጥፋተኛ የተባሉት ዶናልድ ትራምፕ የፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ቅስቀሳቸውን እንደቀጠሉ ናቸው
ዶናልድ ትራምፕ ምክትላቸው ጥቁር አሜሪካዊ አልያም ሴት እንደሚያደርጉ ይጠበቃል
ዶናልድ ትራምፕ ስምንት እጩ ምክትል ፕሬዝዳንቶችን አጩ።
ዶናልድ ትራምፕ በቀጣዩ ሕዳር ወር ላይ በሚካሄደው የአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ላይ ሪፐብሊካን ፓርቲን ወክለው እንደሚወዳደሩ ይጠበቃል።
አስገድዶ ደፈራ እና ግብር መሰወርን ጨምሮ በተለያዩ ወንጀሎች ተጠርጥረው ክስ የተመሰረተባቸው ዶናልድ ትራምፕ እጩ ምክትል ፕሬዝዳንት በቅርቡ እንደሚመርጡ አስታውቀዋል።
በአሜሪካ ፖለቲካ የመራጮችን ድምጽ ለማግኘት በሚል ከምርጫ በፊት የምክትል ፕሬዝዳንትን ማንነት ማሳወቅ የተለመደ ነው።
ዶናልድ ትራምፕም ለዚህ እንዲረዳቸው ስምንት እጩ ምክትል ፕሬዝዳንት ያሳወቁ ሲሆን የእጩዎች ገንዘብ ሁኔታ፣ ፈቃደኝነት እና ሌሎች መረጃዎች እየተሰባሰቡ እንደሆነ ተገልጿል።
ትራምፕ በስልጣን ዘመናቸው እንዲታገድ የወሰኑበትን ቲክቶክ ተቀላቀሉ
እንደ ቢቢሲ ዘገባ ዶናልድ ትራምፕ በስልጣን ላይ ያሉት ፕሬዝዳንት ጆ ባይደንን ለመፎካከር ምክትል ፕሬዝዳንታቸውን ጥቁር አልያም ሴት ሊያደርጉ እንደሚችሉ ተገምቷል።
የመጀመሪያው እጩ ምክትል ፕሬዝዳንት ቲም ስኮት ሲሆን ይህም የጥቁር አሜሪካዊያንን ድምጽ ለማግኘት ይረዳል ተብሏል።
ሁለተኛው እጩ የኖርዝ ዳኮታው ሴናተር ዱግ በርገም ሲሆን የኒዮርኳ ኢሊዝ ስቴፋንክ ሌላኛዋ የዶናልድ ትራምፕ እጩ ምክትል ፕሬዝዳንት ዝርዝር ውስጥ ተካታለች።
የፍሎሪዳው ሴናተር ማርክ ሩቢዮ ሌላኛው እጩ ምክትል ፕሬዝዳንት ተደርጎ ከተያዙት ፖለቲከኞች መካከል ሲሆን የላቲን ቋንቋ ተናጋሪ መራጮችን ለማግኘት እንደሚረዳቸው ተገምቷል።
የካፒታሊስ ጽንሰ ሀሳብ ተሟጋቹ እና ደራሲው ጄዲ ቫንስ ሌላኛው በዶናልድ ትራምፕ የተያዘ እጩ ምክትል ፕሬዝዳንት ሲሆን በተለይም የተማሩ አሜሪካዊያንን ድምጽ እንዲያገኙ ሊረዳቸው ይችላል ተብሏል።
የፖለቲካ ተንታኟ ክርስቲ ኖኢም የዶናልድ ትራምፕ ምክትል ፕሬዝዳንት ለመሆን ፈቃደኛ ሆናለች የተባለ ሲሆን ሌላኛው ጥቁር አሜሪካዊ እና የባንክ ባለሙያው ቢሮን ዶናልድስ የዶናልድ ትራምፕን ትኩረት መሳቡ ተገልጿል።
ከሕንድ ቤተሰቦች የተወለደችው ቱልሲ ጋባርድ በዶናልድ ትራምፕ አይን ውስጥ የገባች ፖለቲከኛ ስትሆን በተለይም በአሜሪካ የሚኖሩ ህንዳዊያንን መራጮች ድምጽ እንዲያገኙ ሊረዳቸው ይችላል ተብሏል።
የአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጭ የፊታችን ሕዳር አምስት እንደሚካሄድ የተገለጸ ሲሆን ጥር ወር ላይ ደግሞ ምርጭ ያሸነፈው ተመራጭ ፕሬዝዳንት ቃለ መሀላ ፈጽሞ ስራ ይጀምራል።