ሩሲያ በዩክሬን ድንበር የምታደርገው እንቅስቃሴ ያሳሰባቸው ባይደን ከአውሮፓ መሪዎች ጋር ተወያዩ
መሪዎቹ፤ ሩሲያ በዩክሬን ድንበር አቅራቢያ ያለውን ውጥረት እንድታረግብም ጠይቀዋል
ከሩሲያ በኩል የተሰጠ አስተያየት የለም
ሩሲያ በዩክሬን ድንበር የምታደርገው እንቅስቃሴ ያሳሰባቸው የአሜሪካው ፐሬዚዳንት ጆ ባይደን ከአውሮፓ ሀገራት መሪዎች ጋር መነጋገራቸው ተገልጸ።
ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ከፈረንሳይ፣ ጀርመን፣ ጣሊያን እና ብሪታኒያ መሪዎች ጋር በስልክ እንደተወያዩ ነው የተገለጸው።
- ኔቶ በዩክሬን ጉዳይ ቀይ መስመር ካለፈ ሩሲያ እርምጃ ትወስዳለች- ፕሬዝዳንት ፑቲን
- ኔቶ በዩክሬን ጉዳይ ቀይ መስመር ካለፈ ሩሲያ እርምጃ ትወስዳለች- ፕሬዝዳንት ፑቲን
በዚህም መሰረት የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ባይደን ውይይት ያደረጉት ከፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን፣ ከጀርመኗ መራሄተ መንግስት አንጌላ ሜርክል ከጣሊየኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ማሪዮ ድራጊ እንዲሁም ከብሪታኒያው ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ጋር ነው።
መሪዎቹ ሩሲያ፤ በዩክሬን ድንበር ላይ ያደረገችው ወታደራዊ ዝግጁነት እንደሚያሳስባቸው መምከራቸውን ሲጂቲኤን ዘግቧል።
የሀገራቱ መሪዎች ለዩክሬን ሉዓላዊነት እና ግዛታዊ አንድነት ያላቸውን ድጋፍ አስምረውበታል ነው የተባለው።
ጆ ባይደን፣ ኢማኑኤል ማክሮን፣ አንጌላ ሜርክል፣ ማሪዮ ድራጊ እና ቦሪስ ጆንሰን፤ ሩሲያ በአካባቢው ያለውን ውጥረት ማርገብ እንዳለባት ጥሪ አቅርበዋል።
የአሜሪካ እና የአውሮፓ ሀገራት መሪዎችን ንግግር በተመለከተ ከክሬምሊን በኩል የተሰጠ አስተያየት እስካሁን አልተሰማም።
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ከሩሲያው አቻቸው ቭላድሚር ፑቲን ጋር ዛሬ በበይነ መረብ አማካኝነት በዛሬው እለት ውይይት እንደሚያደርጉም ይጠበቃል።