ፖለቲካ
ሩሲያ፤ ምእራባውያን “ቀይ መስመር እንዳያልፉ ያስጠነቀቁትን ከቁብ አልቆጠሩትም” አለች
ሞስኮ ከፀጥታ ጋር በተያያዘ ከምዕራባውያን ትክክለኛ ኃላፊነት እንደምትፈልግ አስታውቃለች
ምእራባውያንም በቤላሩስ የስደተኞች ቀውስ እንዲፈጠር ማድረጋቸውንም ፕሬዝዳንት ፑቲን ጠቅሰዋል
ምዕራባውያን የሩሲያን ቀይ መስመር እንዳያልፉ ያስጠነቀቀችውን መልዕክት ከቁብ አለመቁጠራቸውን የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት አስታወቁ።
ቭላድሚር ፑቲን ምዕራባውያን የሞስኮን ቀይ መስመር እንዳያልፉ ብታስጠነቅቅም እነሰርሱ ግን በበቂ ሁኔታ በቁም ነገር እንዳልያዙት ገልጸዋል።
አሁን ላይ ሞስኮ ከምዕራባውያን ትክክለኛ የጸጥታ ኃላፊነት እንደምትፈልግ ተናግረዋል፡፡
ፕሬዝዳንቱ በሞስኮ ለለውጭ ፖሊሲ ባለስልጣናት በሰጡት ገለጻ በምስራቅ ዩክሬን ያለውን ግጭት ለመፍታት የተሄደው ርቀት ተስፋ ሰጭ እንዳልሆነም ገልጸዋል።
ምዕራባውያንም በቤላሩስ የስደተኞች ቀውስ እንዲፈጠር ማድረጋቸውንም ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጠቅሰዋል።
የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) እና ሩሲያ ያላቸው ግንኙነት የተበላሸ ሲሆን ግንኙነቱን ለማሻሻልም ያሉትን ዕድሎች ራሱ ኔቶ እንዳበላሻቸውም ነው ፑቲን የገለጹት።