ሩሲያ የአውሮፓ ምድር “ወደ ወታደራዊ ፍጥጫ እየተመለሰ እንዳይሆን?” ስትል አስጠነቀቀች
ላቭሮቭ "የመካከለኛ ርቅት ተዝመዘግዘጊ ሚሳኤሎች ወደ አውሮፓ እየመጡ ነው"ብለዋል
ሩሲያ 90ሺ ወታዶሮቿን ወደ ዩክሬን ማስጠጋቷና ኔቶ ጦሩን በፖላንድ እና ዩክሬን ማስጠጋቱ ጉዳዩ አሳሳቢ አድርጎታል
የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒሰትር ሰርጌ ላቭሮቭ የአውሮፓ ምድር “ወደ ወታደራዊ ፍጥጫ እየተመለሰ እንዳይሆን ?” አስጠነቀቁ፡፡
ሚኒስትሩ ይህንን ያሉት በስዊድን እየተካሄደ ባለውና “የአውሮፓን የደህንነት ጉዳይ” ማጠንጠኛው ባደገው ጉባኤ ላይ ነው፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ላቭሮቭ ፤" ኔቶ ኃላፊነት ባልተሞላበት መልኩ ወታደሮቹን በፖላንድ እና ሮማንያ በኩል ወደ ሩስያ ድንበሮች እያስጠጋ ነው" ሲሉ ከሷል።
ላቭሮቭ አክለው "የመካከለኛ ርቅት ተዝመዘግዘጊ ሚሳኤሎች ወደ አውሮፓ እየመጡ ነው፤ ይህ ዳግም ወደ ወታደራዊ ፍጥጫ የሚመልስ ነው" ብለዋል፡፡
ኔቶ የሩሲያ አጎራባች ሀገራትን እንደ "የፍጥጫ ድልድይ" አድርጎ ከመጠቀም ሊታቀብ ይገባል ሲሉም አስጠንቅቀዋል ላቭሮቭ፡፡
ላቭሮቭ አሁን ላይ ወደ ወታደራዊ ፍጥጫ ማቅናቱ ሊሆንና ሊታሰብ የማይችል ቅዠት ነው ሲሉም ነው የተደመጡት፡፡
ሚንስተሩ የሰሜን አትላንቲክ ስምምነት ድርጅት ወደ ምእራብ የሚደርገውን መስፋፋት ለማስቆም “አዲስ አውሮፓዊ ስምምነት ድርጅት” ማቋቋም ያስፈልጋል የሚል ምክረ ሀሳብም አቅርቧል፡፡
የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን፡ ሩሲያ ከዩክሬን ጋር ወደ ግጭት ከገባች "ከባድ ዋጋ ሊያስከፍላት እንደሚችል" ከቀናት በፊት ማስጠንቀቃቸው የሚታወስ ነው፡፡
ነገሮች እንዲህ በተካረሩበት ወቅት ሩሲያ 90 ሺ ወታዶሮቿን ወደ ዩክሬን ማስጠጋቷንም ታድያ ጉዳዩን አሳሳቢ አድርጎታል፡፡
ከላቭሮቭ ጋር በጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡት የአሜሪካው አቻቸው ብሊንክን ግን የሚያዋጠው መንገድ ዲፕሎማሲ ብቻ መሆኑ በማሳወቅ፤ ሩስያ ጦሯን ካስገባቸውባቸው የዩክሬን አከባቢዎች እንድታስወጣ ጠይቋል፡፡
ሞስኮ በሺዎች የሚቆጠሩ ወታደሮቿ ወደ ዩክሬን ብታስጠጋም ግን፤ በአሜሪካ በኩል “ዩክሬንን ልታጠቃ ጥችላለች” በሚል የሚቀርበው ክስ ውድቅ አድርጋለች፡፡
በአንጻሩ ዩክሬን ራሷ ጦርነት ለመክፈት በከፍተኛ ደረጃ ወታደራዊ ዝግጅት በማድረግ ላይ ናት ስትልም ትከሳለች ሩሲያ፡፡ሩስያ ሃሙስ እለት የዩክሬን ሰላዮች ናቸው ያለቻቸው ሶስት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ማዋሏምንም ገልጻለች፡፡የሩሲያ ጸጥታ ጉዳዮች አገልግሎት ፡በቁጥጥር ስር ከዋሉት ተጠርጣሪዎች አንዱ፤ የሽብር ጥቃት ሊፈጽም ነበር በሚል የተከሰሰ ሲሆን ሌሎቹ ሰላዮች ናቸው ብሏል፡፡
በስዊድን እየተካሄደ ባለው ጉባኤ ሰርጌ ላቭሮቭ እና አንቶኒ ብሊንከንን ጨምሮ የበርካታ ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒሰትሮች የተገኙበት ነው፡፡
ሰርጌ ላቭሮቭ እና አንቶኒ ብሊንከን በዩክሬን ጉዳይ ውይይት ለማድረግ ከመግባባት ላይ መድረሳቸውንም ነው የተሰማው፡፡ከሚኒትሮቹ ባሻገር የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቪላድሚር ፑቲን እና የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ-ባይደን በቅረቡ ሊገናኙ እንደሚችሉም ብሊንከን ጠቁሟል፡፡
ከብሊንከን በተጨማሪ መሪዎቹ በቅርብ ቀናት ሊገናኙ እንደሚችሉ ኢንተርፋክስ የተሰኘ የዜና አውታር የሩስያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርን ዋቢ አድርጎ መዘገቡ አይዘነጋም፡፡
መሪዎች በወርሃ ሰኔ/2021 በጀኔቫ ሲገናኙ የዩክሬን ጉዳይ ዋና አጀንዳቸው አድረግው እንደመከሩ የሚታወስ ነው፡፡ፑቲን ሶሞኑን በቴሌቭዥን መስኮት ብቅ