ኔቶ በዩክሬን ጉዳይ ቀይ መስመር ካለፈ ሩሲያ እርምጃ ትወስዳለች- ፕሬዝዳንት ፑቲን
ፕሬዝዳንት ፑቲን ምዕራባውያን በዩክሬን በሚያደርጉት ወታደራዊ እንቅስቃሴ ላይ ቅሬታቸውን አስምተዋል
ከባድ መሳሪያዎችን ወደ ዩክሬን ማስገባት “ቀይ መስመር” ነው ሲሉም አስታውቀዋል
ሩሲያ” የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪካን (ኔቶ) በዩክሬን ጉዳይ ላይ ያስቀመጥኩትን ቀይ መስምር ከጣሰ እርምጃ ለመውሰድ እገደዳላሁ” አለች።
የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጉዳዩን አስመልክቶ ትናንት በሰጡት አስተያየት፤ ሞስኮ ምዕራባውያን ወደ ዩክሬን የኒኩሌር አረር ተሸካሚ ሚሳዔሎችን ለማስገባት የሚደርጉትን ሂደቶችን በቅርበት እየተከታተለች ነው ብለዋል።
በሞስኮ በተካሄደው የኢንቨስትመንት ፎረም ላይ ንግግር ያደረጉት ፕሬዝዳንት ፑቲን፤ በጋራ መንፈስ መስራት ለሁሉም እንደሚጠቅም አስታውቀው፤ ነገር ግን ኔቶ በዩክሬን አካባቢ የሚያደርጋው እንቅስቃሴዎች በሩሲያ ደህንነት ላይ አደጋ የሚደቅን እንዳይሆን አሳስበዋል።
ምዕራባውያን የኬይቭን ወታደራዊ አቅም እና መሰረተ ልማት ማስፋፋታቸውን ከቀጠሉ ግን ሩሲያ ምለሽ ለመልጠት እንደምትገደድም ነው ፕሬዝዳንቱ ያስታወቁት።
በዩክሬን ድንበር ውስጥ ለጥቃት የሚውል ከባድ የጦር መሳሪያ ከገባ ሞስኮን ለመውጋት ከ7 እስከ 10 ደቂቃ ብቻ በቂ መሆኑን ያነሱት ፕሬዝዳንቱ፤ “ሀይፐርሶኒክ መሳሪያዎች ወደ ዩክሬን ከገቡ ደግሞ 5 ደቂቃ በቂ ነው” ብለዋል።
“ለእነደዚህ አይነት ቢሆን ምን ማድረግ አለብን?” ለሚለውም ሩሲያ በዚህ መንገድ ለሚፈታተኗት ተመሳሳይ ነገር ማዘጋጀት አለባት ያሉ ሲሆን፤ “ይህንንም አሁኑኑ ማድረግ እንችላለን” ሲሉም ተናግረዋል።
ፕሬዝዳንት ፑቲን አክለውም ሩሲያ በባህር ስር የሚጓዝ በጣም ፈጣን የሆነ ሀይፐርሶኒክ ሚሳኤል ሙከራ ማድጓን አስታውቀው፤ ሚሳኤሉ በአዲሱ የፈረንጆች ዓመት ወደ ስራ የሚገባ መሆኑንም አስታውቀዋል።
የአዲሱ ሚሳኤል የውጊያ ጊዜ 5 ደቂቃ መሆኑን ያሱት ፕሬዝዳንቱ፤ ፍጥነቱም ከድምጽ በ9 እጥፍ የሚበልጥ እንደሆነም ገልፀዋል።
አሜሪካ እና ብሪታኒያ ባሳለፍነው ማከሰኞ በዩክሬን ካለው ወታደራዊ ውጥረት ጋር በተያያዘ ሩሲያን ማስጠንቀቃቸው የሚታወስ ሲሆን፤ ሩሲያ በደቡባዊ ዩክሬን ጦሯን ማስጠጋቷን ተከትሎም ከኔቶ ጋር መወያየታው ይታወሳል።